Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 15:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እርሱም “የተላክሁት ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች ነው እንጂ ለሌላ አይደለም” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እርሱም፣ “የተላክሁት ከእስራኤል ቤት ሆነው ወደ ጠፉት በጎች ብቻ ነው” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እርሱም “እኔ የተላክሁት ከእስራኤል ቤት እንደ በጎች ለጠፉት ብቻ ነው” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እርሱም መልሶ “ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም፤” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እርሱም መልሶ፦ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።

参见章节 复制




ማቴዎስ 15:24
13 交叉引用  

እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ ጌታም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።


የጠፋውን እፈልጋለሁ፥ የባዘነውን እመልሳለሁ፥ የተሰበረውንም እጠግናለሁ የደከመውንም አበረታለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውን አጠፋለሁ፤ በፍትሕም እጠብቀዋለሁ።


በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም ባርያዬ ዳዊት ነው፤ ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል።


እርሱ ግን አንድ ቃልም አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ከኋላችን እየጮኸች ነውና አሰናብታት” እያሉ ለመኑት።


የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ለማዳን ነው።


ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ አዘነላቸው፥ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀውና ተጥለው ነበርና።


ጳውሎስና በርናባስም ገልጠው “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ ይነገር ዘንድ ያስፈልጋል፤ ከገፋችሁትና የዘለዓለም ሕይወት እንዳይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን፥ እነሆ፥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን።


ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ሊያጸና፤ ስለ እግዚአብሔር እውነት ክርስቶስ ለተገረዙት አገልጋይ ሆነ እላለሁ፤


跟着我们:

广告


广告