Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 5:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ልጅቱም ወዲያውኑ ተነሥታ ቆመች፤ መራመድ ጀመረች፤ ዕድሜዋም ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ ሰዎቹም እጅግ በመደነቅ ተደመሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ብላቴናዪቱም ወዲያውኑ ተነሥታ ቆመች፤ ወዲያ ወዲህም ሄደች። ዕድሜዋም ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር። ሰዎቹም በሁኔታው እጅግ ተደነቁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 እርስዋ የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ስለ ነበረች ወዲያውኑ ተነሥታ ወዲያና ወዲህ ማለት ጀመረች፤ ይህም በሆነ ጊዜ ሰዎቹ እጅግ ተደነቁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ብላቴናይቱም የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረችና ወዲያው ቆማ ተመላለሰች። ወዲያውም ታላቅ መገረም ተገረሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ብላቴናይቱም የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረችና ወዲያው ቆማ ተመላለሰች። ወዲያውም ታላቅ መገረም ተገረሙ።

参见章节 复制




ማርቆስ 5:42
7 交叉引用  

ሕዝቡ በሙሉ በመደነቅ፥ “ይህ ምንድነው? በሥልጣን ርኩሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል፤ ይህ አዲስ ትምህርት ምንድነው?” እያሉ እርስ በርስ ተጠያየቁ።


እጅግም ፈሩና “እንዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።


ከዚያም የልጅቱን እጅ ይዞ፥ “ጣሊታ ቁሚ” አላት፤ ትርጉሙም፥ “አንቺ ልጅ ተነሺ” ማለት ነው።


እርሱም ይህን ነገር ማንም እንዳያውቅ አጥብቆ አስጠነቀቃቸው፤ የሚበላ ነገር እንዲሰጧትም ነገራቸው።


እርሱም በጀልባዋ ላይ ወጥቶ አብሯቸው ሆነ፤ ነፋሱም ፀጥ አለ፤ እነርሱም እጅግ ተደነቁ፤


ሕዝቡም ከመጠን በላይ በመደነቅ፥ “ያደረገው ሁሉ ጥሩ ነው፤ ደንቆሮዎች እንዲሰሙ፥ ድዳዎች እንዲናገሩ እንኳን አድርጓል” አሉ።


跟着我们:

广告


广告