ሚልክያስ 1:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ወድጃችኋለሁ ይላል ጌታ፤ እናንተ ግን፦ “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል ጌታ። ሆኖም ያዕቆብን ወደድኩት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 “እኔ ወድጃችኋለሁ” ይላል እግዚአብሔር። “እናንተ ግን፣ ‘እንዴት ወደድኸን?’ ትላላችሁ።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ያዕቆብን ወደድሁ፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እግዚአብሔር ሕዝቡን “እኔ እናንተን ወድጄአችኋለሁ” ይላል። እናንተ ግን “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፥ “ዔሳውና ያዕቆብ ወንድማማቾች ነበሩ፤ እኔ ግን ያዕቆብን ወደድኩ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ፥ 参见章节 |