Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 8:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 ከበስተኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ ወዲያውም ደምዋ መፍሰሱን አቆመ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 እርሷም ከበስተኋላው ተጠግታ የልብሱን ጫፍ ነካች፤ የሚፈስሰው ደሟም ወዲያውኑ ቆመ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 እርስዋ ወደ ኢየሱስ መጥታ ከበስተኋላው ቀረበችና የልብሱን ጫፍ ነካች፤ ወዲያውኑ ደምዋ መፍሰሱን አቆመ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ቀር​ባም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ በስ​ተ​ኋ​ላው ቆመ​ችና የል​ብ​ሱን ጫፍ ዳሰ​ሰች፤ ያን​ጊ​ዜም የደ​ምዋ መፍ​ሰስ ቆመ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 በኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፥ የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ።

参见章节 复制




ሉቃስ 8:44
15 交叉引用  

እርሱም፦ “አንተ የጌታ አምላክህን ቃል ብትሰማ፥ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላመጣብህም፤ ፈዋሽህ እኔ ጌታ ነኝና” አለ።


ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ ከጋጣ እንደ ወጡ ጥጃዎች ትቦርቃላችሁ።


ኢየሱስም አዘነላቸውና ዐይኖቻቸውን ዳሰሰ፤ ወዲያውኑ አዩ፥ ተከተሉትም።


እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ” አለው። ወዲያውም ለምጹ ነጻ።


እነሆ ለዐሥራ ሁለት ዓመታት ደም የሚፈስሳት ሴት ከኋላው ተጠግታ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤


በየደረሰበት መንደር ወይም ከተማ ወይም ገጠር ሁሉ ሕመምተኞችን በየአደባባዩ እያስቀመጡ የልብሱን ጫፍ እንኳን ለመንካት ይለምኑት ነበር፤ የነኩትም ሁሉ ይድኑ ነበር።


እጁንም ጫነባት፤ ያን ጊዜም ቀጥ አለች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።


በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ፥ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፤ በራስ ጠጉርዋም ታብሰው፥ እግሩንም ትስመው፥ ሽቶም ትቀባው ነበረች።


ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤ ያላትንም ንብረት ሁሉ ተጠቅማ ለባለመድኃኒቶች ብታውልም ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።


ኢየሱስም፦ “ማን ነው የነካኝ?” አለ። ሁሉም በካዱ ጊዜ፥ ጴጥሮስ፦ “አቤቱ! ሕዝቡ በዙሪያህ ከበውህ እየተጋፉህ እኮ ነው!” አለ።


ዳሩ ግን የተፈወሰው ሰው ማን እንደሆነ አላወቀም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ፈቀቅ ብሎ ስለ ነበርና፥ በዚያ ስፍራ ብዙ ሰዎች ሰለ ነበሩ ነው።


ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮችይወስዱ ነበር፤ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር።


ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።


“በምትለብሰው በልብስህ በአራቱ ማዕዘን ዘርፍ አድርግ።


跟着我们:

广告


广告