Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 5:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እንዲህ ሲልም በምሳሌ ነገራቸው፦ “የአዲስ ልብስ እራፊን ቀድዶ ባረጀ ልብስ ላይ የሚያኖር ማንም የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱን ይቀደዋል፤ አዲሱም እራፊ ለአሮጌው አይስማማውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ደግሞም እንዲህ ሲል ምሳሌ ነገራቸው፤ “ከአዲስ ልብስ ላይ ቍራጭ ጨርቅ ቀድዶ በአሮጌ ልብስ ላይ የሚጥፍ ማንም የለም፤ እንዲህ ቢደረግ አዲሱ ልብስ ይቦጨቃል፤ አዲሱም ዕራፊ ለአሮጌው ልብስ አይስማማውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ቀጥሎም ኢየሱስ፥ እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፦ “የአዲስ ልብስ ዕራፊ በአሮጌ ልብስ ላይ የሚጥፍ ማንም የለም፤ ይህን ቢያደርግ ግን አዲሱን ልብስ ይቀደዋል፤ አዲሱም ዕራፊ ለአሮጌው ልብስ አይስማማም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 በም​ሳ​ሌም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በአ​ሮጌ ልብስ ቀዳዳ ላይ የአ​ዲስ ልብስ እራፊ የሚ​ጥፍ የለም፤ ያለ​ዚያ ግን አዲሱ አሮ​ጌ​ውን ይቀ​ድ​ደ​ዋል፤ አዲሱ እራ​ፊም ከአ​ሮ​ጌው ጋር አይ​ስ​ማ​ማም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ደግሞም ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፦ የአዲስ ልብስ እራፊ ባረጀ ልብስ ላይ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱን ይቀደዋል ደግሞም አዲስ እራፊ ለአሮጌው አይስማማውም።

参见章节 复制




ሉቃስ 5:36
7 交叉引用  

“ሥርዓቴን ጠብቁ። እንስሳህን ከሌላ ዓይነት ዘር ጋር አታዳቅል፤ በእርሻህም ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ፤ ከሁለት ዓይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።”


ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ቀኖች ይመጣሉ፤ በነዚያ ቀኖች ይጾማሉ።”


ባረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር ማንም የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱ የወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፤ እርሱም ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከጥቅም ውጪ ይሆናል።


የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።


“ሱፍና በፍታ ተቀላቅሎ አብሮ የተሠራ ልብስ አትልበስ።


跟着我们:

广告


广告