Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 5:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎችን ልታጾሙ አትችሉም፤ ትችላላችሁን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ሙሽራው ዐብሯቸው እያለ ዕድምተኞቹ እንዲጾሙ ማድረግ ይቻላልን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ ሚዜዎች መጾም ይገባቸዋል ብላችሁ ታስባላችሁን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሙ​ሽ​ራው ሚዜ​ዎች ሙሽ​ራው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሳለ መጾም አይ​ች​ሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ኢየሱስም፦ ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎችን ልታስጦሙ ትችላላችሁን?

参见章节 复制




ሉቃስ 5:34
18 交叉引用  

እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ አስምላችኋለሁ፥ ውዴን ያገኛችሁት እንደሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት።


ውድሽ ወዴት ሄደ? አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፥ ከአንቺ ጋር እንፈልገው ውድሽ ወዴት ፈቀቅ አለ?


ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዳጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።


ጎልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፥ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል፤ ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።


ጌታ አምላክሽ በመካከልሽ ኃያል ታዳጊ ነው፤ በአንቺም በፍጹም በደስታ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል።”


“መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ የደገሰ ንጉሥን ትመስላለች።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ እድምተኞች ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ።


እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አዘውትረው ይጾማሉ፤ ጸሎትም ያደርሳሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም።”


ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ቀኖች ይመጣሉ፤ በነዚያ ቀኖች ይጾማሉ።”


ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ።


እንደ አንዲት ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ለማቅረብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር ቅንዐት እቀናላችኋለሁና።


跟着我们:

广告


广告