Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 4:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 አጋንንትም ደግሞ፦ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” ብለው እየጮኹ ከብዙዎች ይወጡ ነበር፤ እርሱ ግን ገሠጻቸው፤ እንዲናገሩም አልፈቀደላቸውም፥ ምክንያቱም ክርስቶስ እንደሆነ አውቀውት ነበርና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 አጋንንትም ደግሞ፣ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” እያሉና እየጮኹ ከብዙ ሰዎች ወጡ። እርሱ ግን ገሠጻቸው፤ ክርስቶስ መሆኑንም ያውቁ ስለ ነበር፣ አንዳች እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 አጋንንትም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” እያሉ በመጮኽ ብዙ ሰዎችን እየለቀቁ ይወጡ ነበር፤ እርሱ መሲሕ መሆኑንም ዐውቀው ነበር፤ ኢየሱስ ግን ስለ እርሱ ምንም እንዳይናገሩ በመገሠጽ ይከለክላቸው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ብዙ አጋ​ን​ን​ትም፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ ነህ” እያ​ሉና እየ​ጮሁ ይወጡ ነበር፤ እር​ሱም ይገ​ሥ​ጻ​ቸው ነበር፤ ክር​ስ​ቶ​ስም እንደ ሆነ ያውቁ ነበ​ርና እን​ዲ​ና​ገሩ አይ​ፈ​ቅ​ድ​ላ​ቸ​ውም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 አጋንንትም ደግሞ፦ አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ እየጮኹም ከብዙዎች ይወጡ ነበር፤ ገሠጻቸውም ክርስቶስም እንደ ሆነ አውቀውት ነበርና እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።

参见章节 复制




ሉቃስ 4:41
14 交叉引用  

ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህኑም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ከሆንህ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ” አለው።


ፈታኙ መጥቶ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው።


በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደሩባቸው ብዙ ሰዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ መናፍስቶቹን ሁሉ በቃል አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።


እነሆ እንዲህ እያሉ ጮኹ “የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?”


ኢየሱስም “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ” አለው።


ኢየሱስም፥ “ጸጥ በል፤ ከእርሱም ውጣ” ብሎ ገሠጸው።


ጀንበር ከጠለቀች በኋላ፥ ምሽት ላይ የአካባቢው ሰዎች ሕመምተኞችንና በአጋንንት የተያዙትን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ።


እርሱም በተለያየ በሽታ የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፤ ብዙ አጋንንትም አወጣ፤ ነገር ግን አጋንንቱ የኢየሱስን ማንነት ያውቁ ስለ ነበር እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።


ርኩሳን መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ተደፍተው፥ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” እያሉ ጮኹ።


በአጠገብዋም ቆሞ ትኩሳቱን ገሠጸውና ለቀቃት፤ ወዲያውም ተነሥታ አገለገለቻቸው።


ነገር ግን ኢየሱስ መሢሕ፥ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።


አንድ እግዚአብሔር እንዳለ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንትም ቢሆኑ ይህንኑ ያምናሉ፤ በፍርሃትም ይንቀጠቀጣሉ።


跟着我们:

广告


广告