Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 20:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አንድ ቀንም ሕዝቡን በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ወንጌልንም ሲሰብክላቸው፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ከሽማግሌዎች ጋር ወደ እርሱ ቀረቡና

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አንድ ቀን ኢየሱስ ሕዝቡን በቤተ መቅደስ ሲያስተምርና ወንጌልን ሲሰብክ የካህናት አለቆች፣ ጸሐፍትና ሽማግሌዎች ተሰብስበው ወደ እርሱ መጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አንድ ቀን ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ተገኝቶ ሕዝቡን ያስተምርና ወንጌልንም ያበሥር በነበረበት ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ሽማግሌዎችም ወደ እርሱ መጡ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ በአ​ንድ ቀን ሕዝ​ቡን በመ​ቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው፥ ወን​ጌ​ል​ንም ሲነ​ግ​ራ​ቸው፥ የካ​ህ​ናት አለ​ቆች፥ ጻፎ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተነ​ሡ​በት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አንድ ቀንም ሕዝቡን በመቅደስ ሲያስተምር ወንጌልንም ሲሰብክላቸው፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ከሽማግሌዎች ጋር ወደ እርሱ ቀረቡና፦

参见章节 复制




ሉቃስ 20:1
10 交叉引用  

በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው “ወንበዴን እንደምትይዙ እኔን ለመያዝ ሰይፍና ዱላ ይዛችሁ ወጣችሁን? ዕለት በዕለት በመቅደስ ተቀምጬ ሳስተምር ሳለሁ አልያዛችሁኝም።


“እስኪ ንገረን፤ እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን ነው የምታደርገው? ወይንስ ይህን ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው?” ብለው ተናገሩት።


ከዚህም በኋላ ኢየሱስ እየሰበከና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች እያበሠረ በየከተማውና በየመንደሩ ያልፍ ነበር፤ ዐሥራ ሁለቱም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤


ኢየሱስም መልሶ “እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም ምንም አልተናገርሁም።


ለሕዝቡም ሲናገሩ የካህናት አለቆችና የመቅደስ አዛዥ ሰዱቃውያንም፥


ሕዝቡንና ሽማግሌዎችንም ጻፎችንም አነሣሡ፤ ቀርበውም ያዙት፤ ወደ ሸንጎም አመጡትና


跟着我们:

广告


广告