Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 13:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ከምሥራቅና ከምዕራብም ከሰሜንና ከደቡብም ይመጣሉ፤ በእግዚአብሔርም መንግሥት በማዕድ ይቀመጣሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ሰዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ መጥተው በእግዚአብሔር መንግሥት በማእድ ይቀመጣሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ብዙ ሰዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ፥ ከሰሜንና ከደቡብ ይመጣሉ፤ በእግዚአብሔር መንግሥትም በማእድ ይቀመጣሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ፥ ከሰ​ሜ​ንና ከደ​ቡብ ይመ​ጣሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥት በማ​ዕድ ይቀ​መ​ጣሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ከምሥራቅና ከምዕራብም ከሰሜንና ከደቡብም ይመጣሉ፥ በእግዚአብሔርም መንግሥት በማዕድ ይቀመጣሉ።

参见章节 复制




ሉቃስ 13:29
14 交叉引用  

ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፥ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።


ሰሜንን፦ “መልሰህ አምጣ፥” ደቡብንም፦ “ልቀቅ፥ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፥ አምጣ እለዋለሁ፤


እርሱም፦ “የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የተረፉትን እንድትመልስ አገልጋዬ እንድትሆን እጅግ ቀላል ነገር ነውና ማዳኔ እስከ ምድር ዳር እንዲደርስ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።


“ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፤ በሁሉም ስፍራ ለስሜ ዕጣን ያመጣሉ፥ ንጹሕ ቁርባንም ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፥” ይላል የሠራዊት ጌታ።


እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፤ ከአብርሃም፥ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋርም በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤


እርሱም መላእክቱን ልኮ ከአራቱ ነፋሳት፥ ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማያት ዳርቻ ምርጦቹን ይሰበስባል።


እነሆም፥ ከኋለኞች ፊተኞች የሚሆኑ አሉ፤ ከፊተኞችም ኋለኞች የሚሆኑ አሉ።”


ሲል መልካም ተናገረ። እንግዲህ ይህ የእግዚአብሔር ማዳን ለአሕዛብ እንደ ተላከ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ እነርሱ ደግሞ ይሰሙታል።


ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት የምትጸኑ ከሆነ ነው፤ ይህም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፤ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።


ይህም ወንጌል ወደ እናንተ ደርሶአል፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ በእውነት ከሰማችሁበትና ካወቃችሁበት ቀን ጀምሮ፥ በእናንተ መካከል እንደ ሆነው እንዲሁ በመላው ዓለም ፍሬ ያፈራል፤ ያድጋልም።


跟着我们:

广告


广告