Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 12:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ጌታም አለ “እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም መጋቢ ማን ነው?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ጌታም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እንግዲህ፣ ምግባቸውን በተገቢው ጊዜ እንዲሰጣቸው፣ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ብልኅ መጋቢ ማነው?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ጌታ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ታዲያ ቤተሰቦቹን በደንብ እንዲያስተዳድርለትና ለአገልጋዮቹም ምግባቸውን በተመደበው ጊዜ እንዲሰጣቸው ጌታው የሚሾመው ታማኝና ብልኅ መጋቢ ማን ነው?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ጌታው በቤ​ተ​ሰቡ ላይ የሚ​ሾ​መው ደግ ታማ​ኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ጌታም አለ፦ እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም መጋቢ ማን ነው?

参见章节 复制




ሉቃስ 12:42
29 交叉引用  

የመቅደሱን ሥራ የሚሠሩ ጠቢባን ሁሉ ሥራቸውን ትተው መጡ፥


ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፥ ልቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።


ሰው በአፉ መልስ ደስ ይለዋል፥ ቃልም በጊዜው ምንኛ መልካም ነው!


በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።


ገና ሳይነጋ ትነሣለች ለቤትዋም ሰዎች ምግባቸውን፥ ለአገልጋዮችዋም ሥራ ትሰጣለች።


የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል።


የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፥ ዳግመኛም አይፈሩምና አይደነግጡም፥ ከእነርሱም አንድም አይጐድልም፥ ይላል ጌታ።


ጮማውን ትበላላችሁ ሱፉንም ትለብሳላችሁ፥ የሰቡትን ታርዳላችሁ፤ መንጋውን ግን አትጠብቁም።


እርሱም “ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀመዝሙር የሆነ ጸሐፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል፤” አላቸው።


በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ ሹሙን ‘ሠራተኞቹን ጥራና ኋላ ከመጡት ጀምረህ መጀመሪያ እስከመጡት ድረስ ደመወዝ ስጣቸው፤’ አለው።


ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባርያ ብፁዕ ነው።


ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና፦ “አታልቅሽ፤” አላት።


“የሚመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ሲል ወደ ጌታ ላካቸው።


በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።


በመልካም የሚያስተዳድሩ፥ በተለይም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙ ሽማግሌዎች፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።


ቃሉን ስበክ፤ ጊዜው ቢመችም ባይመችም ተግተህ ሥራ፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፤ ምከርም።


ኤጲስ ቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ ነቀፋ የሌለበት ሊሆን ይገባዋል፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ፥


ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም። እነርሱ እንደሚጠየቁበት አድርገው ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ፤ ይህንንም በደስታ እንጂ በኀዘን እንዳያደርጉት፥ አለበለዚያ አይጠቅማችሁም።


የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን መሪዎቻችሁን አስቡ፤ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።


ሙሴም ወደ ፊት መባል ለሚገባው ነገር ለመመስከር፥ እንደ አገልጋይ በመላው በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ ነበር፤


የእግዚአብሔርን ልዩ ልዩ ጸጋ መልካም መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ ሌላውን ያገልግል።


跟着我们:

广告


广告