Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 4:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የጉባኤውም ሽማግሌዎች እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ በጌታ ፊት ይጭናሉ፤ ወይፈኑም በጌታ ፊት ይታረዳል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የሕዝቡም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ፊት እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫኑ፤ ወይፈኑም በእግዚአብሔር ፊት ይታረድ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የማኀበሩም አለቆች እጆቻቸውን በኰርማው ራስ ላይ ይጫኑበትና በዚያው በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ይታረድ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የማ​ኅ​በ​ሩም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች እጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ይ​ፈኑ ራስ ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይጭ​ናሉ፤ ወይ​ፈ​ኑ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያር​ዱ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የጉባኤውም ሽማግሌዎች እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ይጭናሉ፤ ወይፈኑም በእግዚአብሔር ፊት ይታረዳል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 4:15
16 交叉引用  

የኃጢአትም መሥዋዕት የሚሆኑትን አውራ ፍየሎች በንጉሡና በጉባኤው ፊት አቀረቡ፥ እጃቸውንም ጫኑባቸው፥ ካህናቱም አረዱአቸው፤


ሙሴንም እንዲህ አለው፦ “አንተ፥ አሮን፥ ናዳብ፥ አቢሁና ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወደ ጌታ ውጡ፥ በሩቁም ስገዱ፤


ሙሴ፥ አሮን፥ ናዳብ፥ አቢሁና ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወጡ፤


“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበሬ መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በጌታ ፊት እንዲሠምርለት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።


እጁንም በሚቃጠለው መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፤ የእርሱንም ኃጢአት ለማስተስረይ የሠመረ ይሆንለታል።


አሮንም ሁለቱን እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ ይጭናል፥ በላዩም የእስራኤልን ልጆች በደል ሁሉ፥ መተላለፋቸውንም ሁሉ፥ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይናዘዛል፤ በፍየሉም ራስ ላይ ያሸክመዋል፥ በተዘጋጀው ሰውም እጅ ወደ ምድረ በዳ እንዲሄድ ያደርገዋል።


የተቀባውም ካህን ከወይፈኑ ደም ወደ መገናኛው ድንኳን ያመጣል፤


ወይፈኑንም ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በጌታ ፊት ያመጣዋል፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናል፥ ወይፈኑንም በጌታ ፊት ያርደዋል።


የኃጢአትንም መሥዋዕት ወይፈን አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በኃጢአቱ መሥዋዕት ወይፈን ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ።


ለሚቃጠል መሥዋዕትም የሚሆን አውራ በግ አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ።


ለቅድስናም የሚሆነውን ሁለተኛውን አውራ በግ አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በሕዝቡ ላይ ሽማግሌዎችና አለቆች እንደ ሆኑ የምታውቃቸውን የእስራኤል ሽማግሌዎች የሆኑ ሰባ ሰዎች ሰብስብልኝ፤ እነርሱንም ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣቸው፥ በዚያም ከአንተ ጋር በየቦታቸው ይቁሙ።


ጌታም በደመናው ውስጥ ሆኖ ወረደ፥ ተናገረውም፥ በእርሱም ላይ ከነበረው መንፈስ ወስዶ በሰባው ሽማግሌዎች ላይ አኖረ፤ መንፈሱም በእነርሱ ላይ ባደረ ጊዜ ትንቢት ተናገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን አልተናገሩም።


ሌዋውያንንም በጌታ ፊት ባቀረብካቸው ጊዜ የእስራኤል ልጆች በሌዋውያን ላይ እጃቸውን ይጫኑባቸው።


ሌዋውያኑም በወይፈኖቹ ራሶች ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ፤ ለሌዋውያንም ማስተስረያ እንዲሆኑ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ለጌታ አቅርብ።


跟着我们:

广告


广告