ዘሌዋውያን 26:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 የቃል ኪዳኑንም በቀል የሚበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተሞቻችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ በመካከላችሁም ቸነፈርን እልክባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 ቃል ኪዳኔን ስላፈረሳችሁ፣ በላያችሁ ሰይፍ በማምጣት እበቀላችኋለሁ፤ በከተሞቻችሁ ውስጥ በምትሰበሰቡበት ጊዜ ቸነፈር እሰድድባችኋለሁ፤ ለጠላትም እጅ ዐልፋችሁ ትሰጣላችሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን በማፍረሳችሁ እናንተን ለመቅጣት ጦርነት አመጣባችኋለሁ፤ በከተሞቻችሁ ብትሰበሰቡም ሊፈወስ የማይችል በሽታ በመካከላችሁ እልካለሁ፤ ለጠላቶቻችሁም እጃችሁን ለመስጠት ትገደዳላችሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 የቃል ኪዳኔንም በቀል ይበቀልባችሁ ዘንድ ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተማችሁም ትሸሻላችሁ፤ ቸነፈርንም እሰድድባችኋለሁ። በጠላቶቻችሁም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 የቃል ኪዳኔንም በቀል ይበቀልባችሁ ዘንድ ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተማችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ ቸነፈርንም እሰድድባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ። 参见章节 |