ዘሌዋውያን 21:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ወይም ከወገቡ የጐበጠ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም የማየት ችግር ያለበት፥ ወይም የእከክ ደዌ ያለበት፥ ወይም ቋቁቻ የወጣበት፥ ወይም የብልቱ ፍሬ የፈረጠ፥ ነውረኛ ሁሉ አይቅረብ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ጐባጣ ወይም ድንክ፣ ማንኛውም ዐይነት የዐይን እንከን ያለበት፣ የሚያዥ ቍስል ወይም እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ አይቅረብ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 በጀርባው ላይ ጉብር ያለበት ወይም ድንክ፥ የዐይን ሕመም ወይም ልዩ ልዩ ዐይነት የቆዳ በሽታ ያለበት፥ ወይም ጃንደረባ የምግብ ቊርባን ለእኔ ለእግዚአብሔር ሊያቀርብ አይገባውም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ወይም ጎባጣ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም ዐይነ መጭማጫ፥ ወይም ቅንድበ መላጣ፥ ወይም እከካም፥ ወይም ቋቍቻም፥ ወይም የአባለዘሩ ፍሬ አንድ የሆነ ነውረኛ ሁሉ አይቅረብ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ወይም ጐባጣ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም ዓይነ መጭማጫ፥ ወይም እከካም፥ ወይም ቍቁቻም፥ ወይም ጃንደረባ፥ ነውረኛ ሁሉ አይቅረብ። 参见章节 |