Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 15:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 “እንዲሁም በመካከላቸው የምትገኘውን የመገናኛዬን ድንኳን በማርከስ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ፥ እናንተ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው ለዩአቸው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 “ ‘በመካከላቸው ያለችውን ማደሪያዬን እንዳያረክሱና በርኩሰታቸው እንዳይሞቱ፣ እስራኤላውያንን ከሚያረክሳቸው ነገር ለዩአቸው።’ ”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 “በመካከላቸው ያለውን ማደሪያዬን በማርከስ እንዳይሞቱ እስራኤላውያንን ከርኲሰት ጠብቃቸው።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 “እን​ዲ​ሁም በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ያለ​ች​ውን ድን​ኳ​ኔን ባረ​ከሱ ጊዜ፥ በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሞቱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው አን​ጹ​አ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እንዲሁም በእነርሱ መካከል ያለችውን ማደሪያዬን ባረከሱ ጊዜ፥ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው ለያቸው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 15:31
22 交叉引用  

በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር።


ደግሞም ይህን አደረጉብኝ፦ በዚያኑ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል፥ ሰንበቶቼንም ሽረዋል።


የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት በምድራቸው በተቀመጡ ጊዜ በመንገዳቸውና በሥራቸው አረከሱአት፥ መንገዳቸው በፊቴ እንደ አደፍ ነበረ።


ሕዝቤን ቅዱስ በሆነውና በረከሰው መካከል እንዲለዩ ያስተምሩ፥ ንጹሕ በሆነውና ንጹሕ ባልሆነው መካከል እንዲለዩ ያሳዩአቸው።


ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር በእድፍሽ ሁሉና በርኩሰትሽም ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ እኔም አሳንስሻለሁ፥ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም።


በዚህም በርኩስና በንጹሕ መካከል፥ በሚበላና በማይበላ ሕይወት ባለው ፍጥረት መካከል ለመለየት ነው።


“ንጹሕ ወይም ርኩስ መሆኑን ለመወሰን እንዲቻል፥ በበግ ጠጉር ልብስ ወይም በበፍታ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከተለፋው ቆዳ በተሠራ በማናቸውም ነገር ላይ የሚወጣ የለምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።”


ፈሳሽ ነገር ላለበት ሰው፥ ዘሩም ለሚፈስስበት በእርሱም ምክንያት ለሚረክሰው ሰው ሕጉ ይህ ነው፤


ሰንበታቴን ጠብቁ፥ ለመቅደሴም ክብርን ስጡ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


መቅደሴን ለማርከስ፥ የተቀደሰውንም ስሜን ለማንቋሸሽ ልጁን ለሞሌክ ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።


ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶቼን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፥ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝና።”


የሞተውን ሰው በድን የነካ ማናቸውም ሰው ሁለመናውን ባያነጻ የጌታን ማደሪያ ያረክሳል፤ ያ ሰው ከእስራኤል ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ በእርሱም ላይ ከርኩሰት የሚያነጻ ውኃ አልተረጨምና ርኩስ ይሆናል፤ ርኩሰቱ ገና በእርሱ ላይ ነው።


“ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለመናውንም ባያነጻ፥ ያ ሰው የጌታን መቅደስ አርክሶአልና ከጉባኤው መካከል ተለይቶ ይጠፋል፤ ከርኩሰት የሚያነጻውን ውኃ አልተረጨም፤ ርኩስ ነው።


ወንዱንና ሴቱን አውጡ፤ እኔ በመካከሉ የማድርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈሩ አወጡአቸው።”


ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነው፤ ይኼውም እናንተ ናችሁ።


“የለምጽ ደዌን በተመለከተ ሌዋውያን ካህናት የሚሰጡህን መመሪያ በትክክል ለመፈጸም ጥንቃቄ አድርግ። እኔ ለእነርሱ የሰጠሁትን ትእዛዝ በጥንቃቄ ተከተል።


እንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፥ የተቀደሰበትን ያንን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቆጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያስቆጣ፥ ቅጣቱ እጅግ የከፋ እንዴት የማይሆን ይመስላችኋል?


አስቀድሞ ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በዝሙት ይለውጣሉ፤ ብቸኛ ንጉሣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።


ስለዚህ ‘የዔሊ ቤት በደል በመሥዋዕትም ሆነ በቁርባን ፈጽሞ አይሰረይም’ ብዬ በዔሊ ቤት ላይ ምያለሁ።”


跟着我们:

广告


广告