ዘሌዋውያን 15:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ፈሳሹም ነገር በሚፈስስበት ጊዜያት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በወር አበባዋ ጊዜ እንደነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ እንደ ወር አበባዋ ርኩስነት ርኩስ ይሆናል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ደሟ መፍሰሱን በቀጠለበት ጊዜ ሁሉ፣ የምትተኛበት ማንኛውም መኝታ ልክ በወር አበባዋ ጊዜ እንደ ነበረው መኝታ ርኩስ ይሆናል፤ የምትቀመጥበትም ማንኛውም ነገር ልክ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ ርኩስ ይሆናል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 በዚህም ጊዜ የምትተኛበትም አልጋ ሆነ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ርኩስ ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ደምዋም በሚፈስስበት ወራት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በግዳጅዋ ጊዜ እንደ ነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ እንደ ግዳጅዋ ርኩስነት ርኩስ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ደምዋም በሚፈስስበት ወራት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በመርገምዋ ጊዜ እንደ ነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ እንደ መርገምዋ ርኩስነት ርኩስ ነው። 参见章节 |