Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 13:59 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

59 “ንጹሕ ወይም ርኩስ መሆኑን ለመወሰን እንዲቻል፥ በበግ ጠጉር ልብስ ወይም በበፍታ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከተለፋው ቆዳ በተሠራ በማናቸውም ነገር ላይ የሚወጣ የለምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

59 ከበግ ጠጕር ወይም ከበፍታ የተሠራ ልብስ ወይም በሸማኔ ዕቃ የተሠራ ወይም በእጅ የተጠለፈ ጨርቅ ወይም ከቈዳ የተሠራ ማንኛውም ዕቃ በደዌ ቢበከል፣ ንጹሕ ወይም ርኩስ መሆኑን ለማወቅ ሕጉ ይህ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

59 ይህ እንግዲህ ከበፍታም ሆነ ከበግ ጠጒር፥ ወይም ከቈዳ በተሠራ ልብስ ላይ በድሩም ሆነ በማጉ በሻጋታ አማካይነት የሚተላለፍ ምልክት ተመርምሮ የሚታወቅበት የሥርዓት መመሪያ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

59 “በበግ ጠጕር ልብስ፥ ወይም በተ​ልባ እግር ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተ​ደ​ረገ ነገር ላይ ቢሆን፥ ንጹሕ ወይም ርኩስ ያሰኝ ዘንድ የለ​ምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

59 በበግ ጠጕር ልብስ ወይም በበፍታ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛ በተደረገ ነገር ላይ ቢሆን፥ ንጹሕ ወይም ርኩስ ያሰኝ ዘንድ የለምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 13:59
12 交叉引用  

“የለምጽም ደዌ በልብስ ላይ ቢወጣ፥ ልብሱም የበግ ጠጉር ወይም በፍታ ቢሆን፥


በድሩ ወይም በማጉ ላይ ቢሆን፥ በፍታ ወይም የበግ ጠጉር ቢሆን፥ በተለፋው ቆዳ ወይም ከተለፋው ቆዳ በተሠራ በማናቸውም ነገር ላይ ቢሆን፥


ነገር ግን አንተ ካጠብኸው ልብስ ወይም ከድሩ ወይም ከማጉ ወይም ከተለፋው ቆዳ ከተሠራ ከማናቸውም ነገር ላይ ደዌው ቢጠፋ፥ ሁለተኛ ጊዜ ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦


“በመንጻቱ ቀን የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ሕግ ይህ ይሆናል፤ ወደ ካህኑ ይወስዱታል።


“ለመንጻቱ የሚቀርበውን ነገር መግዛት አቅሙ ለማይፈቅድለት የለምጽ ደዌ ላለበት ሰው ሕጉ ይህ ነው።”


እንዲሁም አንድ ነገር በሚረክስና በሚነጻ ጊዜ ለማልከት የሚያስችል ነው። ይህ የለምጽ ደዌ ሕግ ነው።”


“እንዲሁም በመካከላቸው የምትገኘውን የመገናኛዬን ድንኳን በማርከስ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ፥ እናንተ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው ለዩአቸው።”


ፈሳሽ ነገር ላለበት ሰው፥ ዘሩም ለሚፈስስበት በእርሱም ምክንያት ለሚረክሰው ሰው ሕጉ ይህ ነው፤


እርሷ በብላቴንነትዋ ጊዜ በአባትዋ ቤት ሳለች በአባትና በልጂቱ መካከል፥ ወይም በባልና በሚስት መካከል እንዲሆን ጌታ ሙሴን ያዘዘው ሥርዓት ይህ ነው።”


ጌታ በሙሴ አንደበት የእስራኤልን ልጆች በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ሜዳ ያዘዛቸው ትእዛዝና ፍርድ እነዚህ ናቸው።


“ሚስት በባልዋ ሥልጣን ሥር እያለች እርሱን ትታ ፈቀቅ በማለት ራስዋን በምታረክስ ጊዜ ያለው የቅንዓት ሕግ ይህ ነው፤


跟着我们:

广告


广告