Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሰቈቃወ 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጋሜል። ቀበሮች እንኳ ጡቶታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፥ የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኝ ሆነች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ቀበሮዎች እንኳን ግልገሎቻቸውን ለማጥባት፣ ጡታቸውን ይሰጣሉ፤ ሕዝቤ ግን በምድረ በዳ እንዳሉ ሰጎኖች፣ ጨካኞች ሆኑ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ቀበሮዎች እንኳን የወለዱአቸውን ከጡታቸው ይመግባሉ፤ ሕዝቤ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጎኖች ጨካኞች ሆነዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ጋሜል። አራ​ዊት እንኳ ጡታ​ቸ​ውን ገል​ጠው ግል​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን አጠቡ፤ የወ​ገኔ ሴት ልጆች ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካ​ኞች ሆኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ጋሜል። ቀበሮች እንኳ ጡቶታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፥ የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካኝ ሆነች።

参见章节 复制




ሰቈቃወ 4:3
14 交叉引用  

በማግስቱ ማለዳ ተነሥቼ ልጄን ለማጥባት ስዘጋጅ የሞተ ሆኖ አገኘሁት፤ ትኲር ብዬ ስመለከተው እኔ የወለድኩት ልጅ አለመሆኑን ተገነዘብኩ።”


ተኩላዎችም በግንቦቻቸው፥ ቀበሮዎችም በተዋቡ ቤተ መንግሥቶቿ ይጮኻሉ፤ ጊዜዋ ቀርቦአል፤ ቀኗም አይራዘምም።


በአዳራሾችዋም እሾህ፥ በቅጥሮችዋም ሳማና አሜከላ ይበቅሉባታል፤ የቀበሮም ማደሪያና የሰጎን ሥፍራ ትሆናለች።


በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ የተወለደው ሕጻን ልጇን ትረሳለች? ርህራሄ አልባስ እስክመሆን ትደርሳለች? አዎን፥ እርሷ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም።


የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፥ ጠላቶቻቸውንና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና ከበባ ሁሉም የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።’


ሬስ። አቤቱ፥ እይ፥ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት፥ ይበላሉን? በውኑ ካህኑና ነቢዩ በጌታ መቅደስ ውስጥ ይገደላሉን?


ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፥ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኗቸው።


ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፥ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፥ ፍርድንም አደርግብሻለሁ፥ ከአንቺም የተረፉትንም ሁሉ ወደ ሁሉም ነፋሳት እበትናለሁ።


የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፤ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ።


የማያስተውሉ፥ የማይታመኑ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት የሌላቸው ናቸው፤


跟着我们:

广告


广告