Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 7:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ዘቦቹ ተቀያይረው የእኩለ ሌሊቱን ጥበቃ በጀመሩበት ጊዜ፥ ጌዴዎንና አብረውት የነበሩት መቶ ሰዎች በሰፈሩ ዳርቻ ደረሱ፤ እነርሱም ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ የያዟቸውንም ማሰሮች ሰበሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ዘቦቹ ተቀያይረው የእኩለ ሌሊቱን ጥበቃ በጀመሩበት ጊዜ፣ ጌዴዎንና ዐብረውት የነበሩት መቶ ሰዎች በሰፈሩ ዳርቻ ደረሱ፤ እነርሱም ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ የያዟቸውንም ማሰሮዎች ሰበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከእኩለሌሊት ጥቂት ቀደም ብሎ፥ ዘብ ጠባቂዎች ከተቀያየሩ በኋላ ጌዴዎንና ከእርሱ ጋር የተመደቡት መቶ ሰዎች ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ እምቢልታዎቻቸውን ነፉ፤ የያዙትንም ማሰሮ ሁሉ ሰባበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ጌዴ​ዎ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት መቶ ሰዎች በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው ትጋት መጀ​መ​ሪያ ዘብ ጠባ​ቂ​ዎች ሳይ​ነቁ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ ቀንደ መለ​ከ​ቶ​ች​ንም ነፉ፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን ማሰ​ሮ​ዎች ሰባ​በሩ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጌዴዎንም ከእርሱም ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች በመካከለኛው ትጋት ትጋቱም በተጀመረ ጊዜ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፥ ቀንደ መለከቶችንም ነፉ፥ በእጃቸውም የነበሩትን ማሰሮች ሰባበሩ።

参见章节 复制




መሳፍንት 7:19
11 交叉引用  

በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ታደቃቸዋለህ።


ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓት ነውና።


ንጋትም በሆነ ጊዜ ጌታ በእሳትና በደመና ዓምድ ሆኖ የግብፃውያንን ሠፈር ተመለከተ፥ የግብፃውያንንም ሠፈር አወከ።


እኩል ሌሊት በሆነ ጊዜ ‘እነሆ ሙሽራው፤ ልትቀበሉት ውጡ’ የሚል ጩኸት ተሰማ።


የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ የሚመጣ መሆኑን እናንተው ራሳችሁ በጥንቃቄ አውቃችኋልና።


“እነሆ እንደ ሌባ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ ኀፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”


ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፍሎ፥ እያንዳንዱን ሰው ቀንደ መለከትና በውስጡ ችቦ ያለበት ባዶ ማሰሮ በእጁ እንዲይዝ አደረገ።


እኔና አብረውኝ ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከቶቻችንን በምንነፋበት ጊዜ እናንተም በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለከቶቻቸሁን እየነፋችሁ፥ ‘ለጌታና ለጌዴዎን’ ብላችሁ ጩኹ።”


በሦስት ቡድን የተከፈሉት ሰዎች ቀንደ መለከቶቻቸውን ነፉ፤ ማሰሮቻቸውንም ሰበሩ፤ ችቦዎቻቸውን በግራ እጆቻቸው፥ ቀንደ መለከቶቻቸውንም በቀኝ እጆቻቸው ይዘው፥ “የጌታና የጌዴዎን ሰይፍ” በማለት ጮኹ።


跟着我们:

广告


广告