Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 21:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በምጽጳ፥ በጌታ ጉባኤ ፊት ያልተገኘ ማንኛውም ሰው መገደል አለበት ብለው እስራኤላውያን ተማምለው ስለ ነበር፥ “ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በጌታ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን አለ?” ሲሉ ጠየቁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በምጽጳ፣ በእግዚአብሔር ጉባኤ ፊት ያልተገኘ ማንኛውም ሰው መገደል አለበት ብለው እስራኤላውያን ተማምለው ስለ ነበር፣ “ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን አለ?” ሲሉ ጠየቁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት ስንሰበሰብ ወደዚያ ያልመጣ ከእስራኤል ነገዶች መካከል አንድ ወገን እንኳ ይገኛልን?” ብለውም ጠየቁ፤ ይህንንም ያሉበት ምክንያት ወደ ምጽጳ ያልሄደ ማንም ሰው ቢገኝ በሞት ለመቅጣት ተማምለው ስለ ነበር ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ ስላ​ል​ወጣ ሰው፥ “እርሱ ፈጽሞ ይገ​ደል” ብለው ታላቅ መሐላ ምለው ነበ​ርና፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ወደ ጉባኤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ወጣ ማን ነው?” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ስላልወጣ ሰው፦ እርሱ ፈጽሞ ይገደል ብለው ታላቅ መሐላ ምለው ነበርና፦ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ ጉባኤ ወደ እግዚአብሔር ያልወጣ ማን ነው? አሉ።

参见章节 复制




መሳፍንት 21:5
8 交叉引用  

የጌታን ሥራ በቸልታ የሚያደርግ ርጉም ይሁን፥ ደም ከማፍሰስም ሰይፉን የሚከለክል ርጉም ይሁን።


እስራኤላውያን በምጽጳ፥ “ከእኛ አንድም ሰው ሴት ልጁን በጋብቻ ለብንያማውያን መዳር የለበትም” በማለት ተማምለው ነበር።


‘ልጁን ለብንያማዊ የሚድር ርጉም ይሁን’ ብለን እኛ እስራኤላውያን ስለ ተማማልን እንግዲህ ልጆቻችንን ልንድርላቸው አንችልም፤


በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ስለ ወንድሞቻቸው ስለ ብንያማውያን በማዘን እንዲህ አሉ፤ “ዛሬ ከእስራኤል ነገዶች አንዱ ታጥቷል፤


የጌታ መልአክ፦ ሜሮዝን እርገሙ፥ ጌታን በኃያላን መካከል ለመርዳት፥ ጌታን ለመርዳት አልመጡምና የተቀመጡባትን ሰዎች ፈጽማችሁ እርገሙ አለ።


ጥንድ በሬዎች ወስዶ ቆራረጠ፤ ሥጋቸውንም በመልእክተኞች እጅ ልኮ፥ “ሳኦልንና ሳሙኤልን የማይከተል ሰው በሬው እንደዚህ ይቆራረጣል!” ሲል በመላው እስራኤል አስነገረ። ታላቅ ፍርሀት ከጌታ ዘንድ በሕዝቡ ላይ ወደቀ፤ ሕዝቡም እንደ አንድ ሰው ሆኖ ወጣ።


ሳኦል፥ “ዛሬ ጠላቶቼን ከመበቀሌ በፊት፥ እስከ ማታ ድረስ እህል የሚበላ ሰው የተረገመ ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አስምሎ ስለ ነበር፥ በዚያች ዕለት የእስራኤል ሰዎች ተጨንቀው ዋሉ፤ ስለዚህ ከሕዝቡ አንድም እህል የቀመሰ አልነበረም።


跟着我们:

广告


广告