Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 20:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ብንያማውያንም ሊገጥሟቸው ወጡ፤ ከከተማይቱም ርቀው እንዲሄዱ ተደረጉ፤ እንደ በፊቱም እስራኤላውያንን ይገድሉ ጀመር። ከዚህ የተነሣም በሜዳው እንዲሁም ወደ ቤቴልና ወደ ጊብዓ በሚወስደው መንገዶች ላይ ሠላሳ ያህል ሰዎች ወድቀው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ብንያማውያንም ሊገጥሟቸው ወጡ፤ ከከተማዪቱም ርቀው እንዲሄዱ ተደረጉ፤ እንደ በፊቱም እስራኤላውያንን ይገድሉ ጀመር። ከዚህ የተነሣም በሜዳው እንዲሁም ወደ ቤቴልና ወደ ጊብዓ በሚወስደው መንገዶች ላይ ሠላሳ ያህል ሰዎች ወድቀው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ብንያማውያን ሠራዊቱን እየተከተሉ በወጡ ጊዜ ከከተማው ርቀው ሄዱ፤ በዋናው መንገድ ላይ እንደበፊቱ በሠራዊቱ ላይ አደጋ መጣል ጀመሩ፤ ወደ ቤትኤልና ወደ ጊብዓ በሚወስዱት መንገዶችና በሜዳው ላይ ሠላሳ እስራኤላውያንን ገደሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 የብ​ን​ያ​ምም ልጆች በሕ​ዝቡ ላይ ወጡ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሸሹ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ጊዜ፥ በአ​ው​ራ​ዎቹ መን​ገ​ዶች፥ አን​ደ​ኛው ወደ ቤቴል፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ወደ ገባ​ዖን ሜዳ በሚ​ወ​ስ​ዱት መን​ገ​ዶች ላይ ሕዝ​ቡን ይመቱ፥ ይገ​ድ​ሉም ጀመር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠላሳ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 የብንያምም ልጆች በሕዝቡ ላይ ወጡ፥ ከከተማይቱም ተሳቡ፥ እንደ ቀድሞውም ጊዜ፥ በአውራዎቹ መንገዶች፥ አንደኛው ወደ ቤቴል ሁለተኛውም ወደ ጊብዓ ሜዳ በሚወስዱት መንገዶች ላይ፥ ሕዝቡን ይመቱ ይገድሉም ጀመር፥ ከእስራኤልም ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎችን ገደሉ።

参见章节 复制




መሳፍንት 20:31
7 交叉引用  

መተላለፊያውን ዐልፈው እንዲህ ይላሉ፤ “በጌባዕ ሰፍረን እናድራለን።” ራማ ደነገጠች፤ የሳኦል ከተማ ጊብዓ ሸሸች።


የጋይም ሰዎች ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ያህል ሰዎችን ገደሉ፤ ከበሩ እስከ ሸባሪም ድረስ አባረሩአቸው በቁልቁለቱም ላይ ሳሉ መቱአቸው፤ የሕዝቡም ልብ ቀለጠ፥ እንደ ውኃም ሆነ።


በጋይና በቤቴልም ውስጥ እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ ሰው አልነበረም፤ ከተማይቱንም ከፍተው ተዉ፥ እስራኤልንም አሳደዱት።


በሦስተኛውም ቀን ብንያማውያንን ለመውጋት ወጡ፤ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሁሉ ጊብዓን ለመውጋት ቦታ ቦታቸውን ያዙ።


ብንያማውያኑ፥ “እንደ በፊቱ ይሄው ድል እያደረግናቸው ነው” አሉ፥ እስራኤላውያንም በበኩላቸው፥ “ወደ ኋላ እያፈገፈግን ከከተማይቱ ወደ መንገዶቹ እንዲርቁ እናድርጋቸው” ይሉ ነበር።


跟着我们:

广告


广告