Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 20:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በዚህ ጊዜ ብንያማውያን፥ እስራኤላውያን ወደ ምጽጳ መውጣታቸውን ሰሙ፤ ከዚያም እስራኤላውያን፥ “ይህ ክፉ ድርጊት እንዴት እንደ ተፈጸመ እስቲ ንገሩን” ተባባሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በዚህ ጊዜ ብንያማውያን፣ እስራኤላውያን ወደ ምጽጳ መውጣታቸውን ሰሙ፤ ከዚያም እስራኤላውያን፣ “ይህ ክፉ ድርጊት እንዴት እንደ ተፈጸመ እስኪ ንገሩን?” ተባባሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚያን ጊዜ የብንያም ነገድ እስራኤላውያን በሙሉ በምጽጳ መሰብሰባቸውን ሰሙ። እስራኤላውያንም “ይህ ክፉ ሥራ የተፈጸመው እንዴት እንደ ሆነ ንገሩን!” አሉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የብ​ን​ያ​ምም ልጆች የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ወጡ ሰሙ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “ይህ ክፉ ነገር እን​ደ​ምን እንደ ተደ​ረገ ንገ​ሩን” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የብንያምም ልጆች የእስራኤል ልጆች ወደ ምጽጳ እንደ ወጡ ሰሙ። የእስራኤልም ልጆች፦ ይህ ክፉ ነገር እንደምን እንደ ተደረገ ንገሩን አሉ።

参见章节 复制




መሳፍንት 20:3
9 交叉引用  

ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፥ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይሄዱና ይጐዳሉ።


ባላጋራህ ለዳኛ፥ ዳኛውም ለሎሌው እንዳይሰጥህ ወደ እስር ቤት እንዳትገባ፤ ከባላጋራህ ጋር በመንገድ አብረኸው ስትሄድ ሳለህ ፈጥነህ ተስማማ፤


በዚያች ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው፤ ከተማይቱን ከነ ሕዝቧና ከነ ቀንድ ከብቷ ፈጽሞ ደምስስ።


የእስራኤል ነገዶች ለመላው የብንያም ነገድ እንዲህ በማለት መልእክተኞች ላኩ፥ “በመካከላችሁ የተፈጸመው ይህ ክፉ ድርጊት ምንድነው?


የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች ሁሉ ቁጥራቸው አራት መቶ ሺህ በሚሆን፥ ሰይፍ በሚመዙ እግረኞች ወታደሮች በሆኑ በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ መካከል ተገኙ።


ስለዚህ የተገደለችው ሴት ባል ሌዋዊ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔና አባቴ በዚያ ለማደር በብንያም ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ መጣን።


跟着我们:

广告


广告