Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 20:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ብንያማውያንም ከመላው የጊብዓ ነዋሪዎች መካከል ከተመረጡት ሰባት መቶ ሰዎች ሌላ፥ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ስድስት ሺህ ሰዎች በአንድ አፍታ ከየከተሞቻቸው በተጨማሪ አሰባሰቡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ብንያማውያንም ከመላው የጊብዓ ነዋሪዎች መካከል ከተመረጡት ሰባት መቶ ሰዎች ሌላ፣ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ስድስት ሺሕ ሰዎች በአንድ አፍታ ከየከተሞቻቸው በተጨማሪ አሰባሰቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በዚያን ቀን ብንያማውያን፥ ከየከተሞቻቸው ኻያ ስድስት ሺህ መሣሪያ የታጠቁ ሰዎችን አሰባሰቡ፤ ይህም ከጊብዓ ኗሪዎች ከተመረጡት ከሰባት መቶ ሰዎች ሌላ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በዚ​ያም ቀን ከየ​ከ​ተ​ማው የመጡ የብ​ን​ያም ልጆች ተቈ​ጠሩ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ከገ​ባ​ዖን ሰዎች ሌላ ሃያ አም​ስት ሺህ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ሰባት መቶ የተ​መ​ረጡ ሰዎች ተቈ​ጠሩ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በዚያም ቀን ከየከተማው የመጡ የብንያም ልጆች ተቈጠሩ፥ ቁጥራቸውም ከጊብዓ ሰዎች ሌላ ሀያ ስድስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፥ ከጊብዓም ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቆጠሩ።

参见章节 复制




መሳፍንት 20:15
9 交叉引用  

“የብንያም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥


ከብንያም ነገድ የተቈጠሩት ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።


ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።


በየወገናቸው የብንያም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።


ስለዚህ እስራኤላውያንን ለመውጋት ከየከተሞቻቸው በአንድነት ወደ ጊብዓ መጡ።


ይሁን እንጂ እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ተበረታትተው በመጀመሪያው ቀን ተሰልፈው በነበረበት ስፍራ ላይ እንደገና ቦታ ቦታቸውን ያዙ።


በዚሁ ጊዜም ብንያማውያን፥ እስራኤላውያንን ሊወጉ ከጊብዓ ወጡ፤ እንደገናም በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ገደሉ።


ጌታም ብንያምን በእስራኤል ፊት መታው፤ በዚያችም ዕለት እስራኤላውያን በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ብንያማውያንን ገደሉ።


跟着我们:

广告


广告