መሳፍንት 19:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ስለዚህ ሁለቱ ለመብላትና ለመጠጣት አብረው ተቀመጡ። የልጂቷም አባት፥ “እባክህ ዛሬም እዚሁ አድረህ ተደሰት” አለው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ስለዚህ ሁለቱ ለመብላትና ለመጠጣት ዐብረው ተቀመጡ። የልጅቷም አባት፣ “እባክህ ዛሬም እዚሁ ዐድረህ ተደሰት” አለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ስለዚህ ሁለቱ ሰዎች ተቀምጠው አብረው ተመገቡ፤ የሴቲቱም አባት ሌዋዊውን “እባክህ ዛሬ ደስ ብሎህ እዚሁ ዕደር” አለው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ሁለቱም በአንድ ላይ ተቀመጡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ የብላቴናዪቱም አባት ሰውዬውን፥ “ዛሬ ደግሞ ከዚህ እደር ልብህንም ደስ ይበለው” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ተቀመጡም በአንድ ላይም በሉ ጠጡም፥ የብላቴናይቱም አባት ሰውዮውን፦ ዛሬ ደግሞ ከዚህ ለማደር፥ እባክህ፥ ፍቀድ፥ ልብህንም ደስ ይበለው አለው። 参见章节 |