መሳፍንት 18:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 የሚኖሩት ከሲዶና በጣም ርቀው ስለ ነበርና ከማንም ጋር ግንኙነት ስላልነበራቸው የሚታደጋቸው አንድም አልነበረም፤ ከተማይቱም የምትገኘው በቤትሮዓብ አጠገብ ነበረ። የዳንም ሰዎች ከተማይቱን እንደገና ሠርተው መኖሪያቸው አደረጓት። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም28 የሚኖሩት ከሲዶና በጣም ርቀው ስለ ነበርና ከማንም ጋራ ግንኙነት ስላልነበራቸው የሚታደጋቸው አንድም አልነበረም፤ ከተማዪቱም የምትገኘው በቤትሮዓብ አጠገብ ነበረ። የዳንም ሰዎች ከተማዪቱን እንደ ገና ሠርተው መኖሪያቸው አደረጓት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 የላይሽ ሕዝብ ከማንም ጋር ግንኙነት ስላልነበራቸውና ከሲዶንም ርቀው ይኖሩ ስለ ነበረ የሚያድናቸው አልተገኘም። ከተማዋ በቤትረሖብ አጠገብ በሚገኝ ሸለቆ ውስጥ ነበረች፤ የዳን ሰዎችም ከተማዋን እንደገና ሠርተው ኖሩባት። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 የሚታደግም አልነበረም፤ ከሲዶና ርቀው ነበርና፥ እነርሱም ከሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት አልነበራቸውምና። እርስዋም በቤትሮአብ አጠገብ ባለች ሸለቆ ውስጥ ነበረች፤ ከተማዪቱንም ሠርተው ተቀመጡባት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ከተማይቱ ከሲዶና ራቅ ያለች ነበረችና፥ እነርሱም ከሌሎች ሰዎች ተለይተው ብቻቸውን ይኖሩ ነበርና የሚታደግ አልነበራቸውም። ሌሳም በቤትሮዖብ አጠገብ ባለች ሸለቆ ውስጥ ነበረች። ከተማይቱንም ሠርተው ተቀመጡባት። 参见章节 |