Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 18:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ከዚያም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ካህኑን ወስደው ወደ ላይሽ በመሄድ፥ በሰላምና ያለ ስጋት ይኖር የነበረውን ሕዝብ በሰይፍ መቱት፤ ከተማይቱንም በእሳት አቃጠሏት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ከዚያም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ካህኑን ወስደው ወደ ላይሽ በመሄድ፣ በሰላምና ያለ ሥጋት ይኖር የነበረውን ሕዝብ በሰይፍ መቱት፤ ከተማዪቱንም በእሳት አቃጠሏት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከዳን የመጡትም ሰዎች ሚካ የሠራውን ጣዖትና ያገለግለው የነበረውን ካህን ይዘው ጸጥ ብሎ ተዝናንቶ ወደ ተቀመጠው ሕዝብ ወደ ላዪሽ መጡ፤ ሕዝቡንም በሰይፍ ፈጁ፤ ከተማይቱንም በእሳት አቃጠሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እነ​ር​ሱም ሚካ የሠ​ራ​ውን ጣዖ​ትና ለእ​ርሱ የነ​በ​ረ​ውን ካህን ይዘው ወደ ሌሳ፥ ጸጥ ብሎ ተዘ​ል​ሎም ወደ ተቀ​መ​ጠው ሕዝብ መጡ፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አ​ቸው፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እነርሱም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ለእርሱ የነበረውን ካህን ይዘው ወደ ሌሳ፥ ጸጥ ብሎ ተዘልሎም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ፥ መጡ፥ በሰይፍም ስለት መቱአቸው፥ ከተማይቱንም በእሳት አቃጠሉአት።

参见章节 复制




መሳፍንት 18:27
8 交叉引用  

ዳን በወገኑ ይፈርዳል፥ ከእስራኤል ነገድ እንደ አንዱ።


ስለ ዳንም እንዲህ አለ፥ “ዳን የአንበሳ ደቦል ነው፥ ከባሳን ዘልሎ ይወጣል።”


በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ ፈጽመውም አጠፉአቸው፤ እስትንፋስ ያለውንም አላስቀሩም፤ አሦርንም በእሳት አቃጠላት።


የዳንም ልጆች ግዛታቸውን መቆጣጠር ባለልቻሉ ጊዜ ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም፤ ሌሼም የነበረውን ስምዋንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት።


እዚያ ስትደርሱም ያለ ሥጋት የሚኖር ሕዝብ፥ እግዚአብሔር በእጃችሁ የሚሰጣችሁን አንዳች ነገር ያልጐደላትን ሰፊ ምድር ታገኛላችሁ።”


የዳን ሰዎች ይህን ብለው መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ሚካም የማይችላቸው መሆኑን በማየት ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ።


ስለዚህ አምስቱ ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ላይሽ መጡ፤ ሲዶናውያን ያለ ስጋት በጸጥታ እንደሚኖሩ ሁሉ፥ በዚያም የሚኖረው ሕዝብ በሰላም እንደሚኖር አዩ። ምድሪቱ አንዳች የሚጐድላት ነገር ባለ መኖሩ ሕዝቡ ባለጸጋ ነበር። እንዲሁም ከሲዶናውያን ርቆ የሚኖር ሲሆን፥ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ግንኙነት አልነበረውም።


ከዚያም ጌዴዎን ተነሣ፤ ከኖባህና ከዮግብሃ በስተ ምሥራቅ የሚኖሩ ዘላኖች የሚሄዱበትን መንገድ ተከትሎ በጠላት ሠራዊት ላይ በድንገት አደጋ ጣለ።


跟着我们:

广告


广告