Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 18:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የዳን ሰዎች፥ “አትሟገተን፤ ያለዚያ የተቈጡ ሰዎች ጉዳት ላይ ይጥሉሃል፤ አንተም ቤተሰብህም ሕይወታችሁን ታጣላችሁ” አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 የዳን ሰዎች፣ “አትሟገተን፤ አለዚያ የተቈጡ ሰዎች ጕዳት ላይ ይጥሉሃል፤ አንተም ቤተ ሰብህም ሕይወታችሁን ታጣላችሁ” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ከዳን የመጡትም ሰዎች “የተቈጡ ሰዎች አደጋ እንዳይጥሉብህና የአንተንና የቤተሰብህን ሕይወት እንዳታጣ በመካከላችን ምንም ድምፅ ባታሰማ ይሻልሃል” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የዳ​ንም ልጆች እን​ዲህ አሉት፥ “የተ​ቈጡ ሰዎች እን​ዳ​ያ​ገ​ኙ​ህና ነፍ​ስ​ህም፥ የቤተ ሰቦ​ች​ህም ነፍስ እን​ዳ​ይ​ጠ​ፋ​ብህ፥ ድም​ፅህ በእኛ መካ​ከል አይ​ሰማ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የዳንም ልጆች፦ የተቈጡ ሰዎች እንዳይወድቁብህ ነፍስህም የቤተ ሰቦችህም ነፍስ እንዳይጠፋብህ፥ ድምፅህን በእኛ መካከል አታሰማ አሉት።

参见章节 复制




መሳፍንት 18:25
6 交叉引用  

ሑሻይም በተጨማሪ እንዲህ አለው፥ “አባትህና ሰዎቹ ብርቱ ጦረኞችና ግልገሎችዋም እንደተነጠቁባት የዱር ድብ አምርረው የሚነሡ መሆኑን ታውቃለህ፤ በተጨማሪም አባትህ በጦር ሜዳ ልምድ ያለው ነው፤ ሌሊቱን ከሠራዊቱ ጋር አያድርም፤


“ፍርዴን ያስቀረ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም ያስመረራት ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን!


ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፥ ዳመናም ይረፍበት፥ የቀን ጨለማ ያሸብረው።


እርሱም፥ “እንዴት፥ ‘ምን ሆንክ’ ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ? የሠራኋቸውን አማልክቴንና ካህኔን ወስዳችሁ ሄዳችኋል፤ ምን የቀረኝ ነገር አለ?” አላቸው።


የዳን ሰዎች ይህን ብለው መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ሚካም የማይችላቸው መሆኑን በማየት ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ።


ሰዎቹ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ነፍሳቸው ተማርራ ሊወግሩት ስለ ተመካከሩ ዳዊት በጣም ተጨነቀ፤ ነገር ግን ዳዊት በአምላኩ በጌታ በረታ።


跟着我们:

广告


广告