መሳፍንት 16:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 ሰዎች በጓዳ ውስጥ ተደብቀው ነበር፤ እርሷም፥ “ሳምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው፤ ሳምሶን ግን ፈትል እሳት ሲነካው እንደሚበጣጠስ ጠፍሮቹን በቀላሉ በጣጠሳቸው፤ ስለዚህ የብርታቱ ምስጢር ምን እንደሆነ ሊታወቅ አልቻለም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ሰዎች በጓዳ ውስጥ ተደብቀው ነበር፤ እርሷም፣ “ሳምሶን ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው፤ ሳምሶን ግን ፈትል እሳት ሲነካው እንደሚበጣጠስ ጠፍሮቹን በቀላሉ በጣጠሳቸው። ስለዚህ የብርታቱ ምስጢር ምን እንደ ሆነ ሊታወቅ አልቻለም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 በሌላ ክፍል ሆነው የሚጠባበቁ ወንዶች ስለ ነበሩ እርሷ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” ስትል ጮኸች፤ እርሱ ግን ፈትል እሳት ሲነካው እንደሚበጣጠስ ጠፍሮቹን በጣጠሳቸው፤ ስለዚህ አሁንም ብርታት የሚያገኝበትን ምሥጢር ገና አልደረሱበትም ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የሚያደቡትም ሰዎች በጓዳዋ ውስጥ ተደብቀው ነበር። እርስዋም፥ “ሶምሶን ሆይ! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። እርሱም ፈትል እሳት በሸተተው ጊዜ እንዲበጠስ ጠፍሩን በጣጠሰው፤ ኀይሉም በምን እንደ ሆነ አልታወቀም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 በጓዳዋም ውስጥ ሰዎች ተደብቀው ነበር። እርስዋም፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። እርሱም የተልባ እግር ፈትል እሳት በሸተተው ጊዜ እንዲበጠስ ጠፍሩን በጣጠሰው፥ ኃይሉም በምን እንደ ሆነ አልታወቀም። 参见章节 |