መሳፍንት 16:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ነገር ግን ሳምሶን እዚያ የተኛው እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነበር፤ ተነሥቶም የከተማይቱን ቅጥር በር ከሁለት መቃኖቸ ጋር መወርወሪያውንና ማያያዣውን ጭምር በሙሉ ነቅሎ በትከሻው ላይ ካደረገ በኋላ፥ በኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኰረብታ ጫፍ ድረስ ተሸክሞት ወጣ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ነገር ግን ሳምሶን እዚያ የተኛው እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነበር፤ ተነሥቶም የከተማዪቱን ቅጥር በር ከሁለት መቃኖቹ ጋራ መወርወሪያውንና ማያያዣውን ጭምር በሙሉ ነቅሎ በትከሻው ላይ ካደረገ በኋላ፣ በኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኰረብታ ጫፍ ድረስ ተሸክሞት ወጣ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ነገር ግን ሶምሶን ከሴቲቱ ጋር ተኝቶ የቈየው እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነበር፤ ከዚያን በኋላ ከመኝታው ተነሣ፤ የከተማይቱን ቅጽር በር፥ ሁለቱን ምሶሶዎችና መቈለፊያዎቹን ሁሉ ፈነቃቀለ፤ ያንን ሁሉ በትከሻው ተሸክሞ ከኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኮረብታ ድረስ ወሰደ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ሶምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ተኛ፤ በእኩለ ሌሊትም ተነሥቶ የከተማዪቱን በር መዝጊያ ያዘ፤ ከሁለቱ መቃኖችና ከመወርወሪያው ጋር ነቀለው፤ በትከሻውም ላይ አደረገ፤ በኬብሮንም ፊት ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ፤ በዚያም ጣለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ሶምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ተኛ፥ እኩለ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ተነሥቶ የከተማይቱን በር መዝጊያ ያዘ፥ ከሁለቱ መቃኖችና ከመወርወሪያውም ጋር ነቀለው፥ በትከሻውም ላይ አደረገ፥ በኬብሮንም ፊት ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ በዚያም ጣለው። 参见章节 |