መሳፍንት 16:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 የጋዛ ሰዎች፥ “ሳምሶን እዚህ ነው!” የሚል ወሬ ደረሳቸው፤ ስለዚህም ሰዎቹ ቦታውን ከበው፤ ሌሊቱን በሙሉ በከተማይቱ ቅጥር በር ላይ አድፍጠው ጠበቊት፤ “በማለዳ እንገድለዋለን” በማለትም ሌሊቱን በሙሉ እንዳደፈጡ አደሩ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 የጋዛ ሰዎች፣ “ሳምሶን እዚህ ነው!” የሚል ወሬ ደረሳቸው፤ ስለዚህም ሰዎቹ ቦታውን ከብበው፤ ሌሊቱን በሙሉ በከተማዪቱ ቅጥር በር ላይ አድፍጠው ጠበቁት፤ “በማለዳ እንገድለዋለን” በማለትም ሌሊቱን በሙሉ እንዳደፈጡ ዐደሩ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 የጋዛም ሰዎች ሶምሶን በዚያ መኖሩን ሰምተው ያንን ቦታ በመክበብ በከተማይቱ በር ሌሊቱን ሙሉ ሲጠብቁት ዐደሩ፤ “እስኪነጋ ጠብቀን እንገድለዋለን” ብለው በማሰብ ሌሊቱን ሙሉ አደፈጡ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ለጋዛ ሰዎችም፥ “ሶምሶን ወደዚህ መጥቶአል” ብለው ነገሩአቸው፤ ከበቡትም። ሌሊቱንም ሁሉ በከተማዪቱ በር ሸመቁበት፥ “ማለዳ እንገድለዋለን” ብለውም ሌሊቱን ሁሉ በዝምታ ተቀመጡ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 የጋዛ ሰዎችም ሶምሶን ወደ ከተማ ውስጥ እንደ ገባ ሰሙ፥ ከበቡትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ በከተማይቱ በር ሸመቁበት፦ ማለዳ እንገድለዋለን ብለውም ሌሊቱን ሁሉ በዝምታ ተቀመጡ። 参见章节 |