Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 12:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከዚያም ዮፍታሔ የገለዓድን ሰዎች አሰባስቦ ከኤፍሬም ጋር ተዋጋ። ኤፍሬማውያን ገለዓዳውያንን፥ “እናንተ ገለዓዳውያን ከኤፍሬምና ከምናሴ የከዳችሁ ናችሁ” ይሏቸው ስለ ነበር በብርቱ መቷቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም ዮፍታሔ የገለዓድን ሰዎች አሰባስቦ ከኤፍሬም ጋራ ተዋጋ። ኤፍሬማውያን ገለዓዳውያንን፣ “እናንተ ገለዓዳውያን ከኤፍሬምና ከምናሴ የከዳችሁ ናችሁ” ይሏቸው ስለ ነበር በብርቱ መቷቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህ በኋላ ዮፍታሔ የገለዓድን ሰዎች አሰባስቦ በኤፍሬም ሰዎች ላይ አደጋ በመጣል ድል አደረጋቸው፤ የኤፍሬም ሰዎች “እናንተ በኤፍሬምና በምናሴ ግዛት ውስጥ የምትኖሩ ገለዓዳውያን ኤፍሬምን ከድታችሁ የመጣችሁ ናችሁ!” ይሉአቸው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዮፍ​ታ​ሔም የገ​ለ​ዓ​ድን ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ከኤ​ፍ​ሬ​ምም ጋር ተዋጋ፤ ኤፍ​ሬ​ምም፥ “ገለ​ዓ​ዳ​ው​ያን ሆይ! እና​ንተ በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ መካ​ከል የተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ከኤ​ፍ​ሬም ሸሽ​ታ​ችሁ ነው” ስላሉ የገ​ለ​ዓድ ሰዎች ኤፍ​ሬ​ምን መቱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ዮፍታሔም የገለዓድን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፥ ከኤፍሬምም ጋር ተዋጋ፥ ኤፍሬምም፦ ገለዓዳውያን ሆይ፥ እናንተ በኤፍሬምና በምናሴ መካከል የተቀመጣችሁት ከኤፍሬም ሸሽታችሁ ነው ስላሉ የገለዓድ ሰዎች ኤፍሬምን መቱ።

参见章节 复制




መሳፍንት 12:4
11 交叉引用  

በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው ጌታ ስም እነግርሃለሁ” አለው።


ይሁዳም፦ “የተሸካሚዎች ኃይል ደክሟል፥ ፍርስራሹም ብዙ ነው፤ ቅጥሩን መሥራት አንችልም” አለ።


የኤፍሬም ልጆች ለውጊያ ታጥቀው ቀስትንም ገትረው በጦርነት ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ።


ክፉ ሰው በከንፈሩ ኃጢአት ይጠመዳል፥ ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል።


የለዘበች መልስ ቁጣን ትመልሳለች፥ ሸካራ ቃል ግን ቁጣን ታስነሣለች።


የገለዓድ አለቆችም፥ “ጌታ ምስክራችን ነው፤ ያልከውንም በእርግጥ እናደርጋለን” አሉት።


እኔም እንደማትረዱኝ በተረዳሁ ጊዜ በሕይወቴ ቈርጬ አሞናውያንን ለመውጋት ተሻገርሁ፤ ጌታም ድሉን ሰጠኝ፤ ታዲያ ዛሬ እኔን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው?”


ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መሻገሪያዎች ያዙ፤ ታድያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፥ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፥


ናባልም ለዳዊት አገልጋዮች እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ለመሆኑ ይህ ዳዊት ማነው? የእሴይስ ልጅ ማን ነው? በአሁኑ ጊዜ ከጌቶቻቸው የሚኰበልሉ አገልጋዮች ብዙ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告