Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 10:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እስራኤላውያንም ጌታን፥ “ኃጢአት ሠርተናል፤ መልካም መስሎ የታየህን አድርግብን፤ እባክህን የዛሬን ብቻ አድነን” አሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እስራኤላውያንም እግዚአብሔርን፣ “ኀጢአት ሠርተናል፤ መልካም መስሎ የታየህን አድርግብን፤ እባክህን የዛሬን ብቻ አድነን” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የእስራኤል ሕዝብ ግን እግዚአብሔርን “በእርግጥ በድለናል፤ አንተ በእኛ ላይ የፈለግኸውን አድርግብን፤ ብቻ እባክህ የዛሬን አድነን” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እኛ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ናል፤ አንተ በፊ​ትህ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን አድ​ር​ግ​ብን፤ ዛሬ ግን እባ​ክህ አድ​ነን” አሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን፦ እኛ ኃጢአትን ሠርተናል፥ አንተ ደስ የሚያሰኝህን አድርግብን፥ ዛሬ ግን፥ እባክህ፥ አድነን አሉት።

参见章节 复制




መሳፍንት 10:15
16 交叉引用  

እንግዲህ በርታ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ ጌታም በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ።”


ከዚያም ዳዊት ለናታን፥ “ጌታን በድያለሁ” አለው። ናታንም እንዲህ አለው፥ “ጌታ ኃጢአትህን አስወግዶልሃል። አንተ አትሞትም፤


ነገር ግን እርሱ፥ ‘ባንተ አልተደሰትሁም’ የሚል ከሆነ፥ እነሆኝ፥ መልካም መስሎ የታየውን ነገር ያድርግብኝ።”


ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ።


ዳዊትም ጋድን፥ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ብዙ ነውና በጌታ እጅ እንውደቅ፤ በሰው እጅ ግን አልውደቅ” አለው።


እርሱም በሰው ፊት እየዘመረ፦ እኔ በድያለሁ፥ ቀናውንም አጣምሜአለሁ፥ የሚገባኝንም ቅጣት አልተቀበልሁም፥


ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።


አቤቱ ጌታ፥ በመከራ ጊዜ ፈለጉህ፥ በገሠጽሐቸውም ጊዜ ልመናቸውን ወደ አንተ አፈሰሱ።


ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ልብ ጣልኸኝ፥ ወንዝም ከበበኝ፥ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ ላይ አለፉ።


እኛ እንዳንጠፋ፥ እግዚአብሔር ራርቶ ከሚነደው ቁጣው ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?


እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ በእጅህ ውስጥ ነን፤ ለዓይንህም መልካምና ቅን የመሰለውን ነገር አድርግብን።”


እነርሱም፥ ‘ጌታን ትተን በዓልንና አስታሮትን በማምለካችን፥ ኃጢአት ሠርተናል። አሁን ግን ከጠላቶቻችን እጅ ታደገን፤ እኛም አንተን እናመልካለን’ ሲሉ ወደ ጌታ ጮኹ።


ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፥ “እርሱ ጌታ ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ።


እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ውሃ ቀድተው በጌታ ፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለትም ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርን በድለናል” አሉ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር።


跟着我们:

广告


广告