Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መሳፍንት 1:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የይሁዳ ሰዎች ከወንድሞቻቸው ከስምዖን ልጆች ጋር ሆነው በጽፋት ከተማ በሚኖሩት ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ከተማይቱንም ፈጽሞ ደመሰሷት፤ ስለዚህ ከተማይቱ ሖርማ ተብላ ተጠራች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የይሁዳ ሰዎች ከወንድሞቻቸው ከስምዖን ልጆች ጋራ ሆነው በጻፋት በሚኖሩት ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ከተማዪቱንም ፈጽሞ ደመሰሷት፤ ስለዚህ ከተማዪቱ ሖርማ ተብላ ተጠራች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የይሁዳ ሕዝብ ከስምዖን ሕዝብ ጋር በአንድነት ዘምተው በጸፋት ከተማ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ድል አደረጉ፤ ከተማይቱንም ፈጽመው ካጠፉአት በኋላ “ሖርማ” ብለው ሰየሙአት፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ይሁ​ዳም ከወ​ን​ድሙ ከስ​ም​ዖን ጋር ሄደ፤ በሴ​ፌት የተ​ቀ​መ​ጡ​ት​ንም ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፤ ፈጽ​መ​ውም አጠ​ፉ​አት፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ስም ሕርም ብለው ጠሩ​አት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ይሁዳም ከወንድሙ ከስምዖን ጋር ሄደ፥ በጽፋት የተቀመጡትንም ከነዓናውያንን መቱ፥ ፈጽመውም አጠፉአት። የከተማይቱንም ስም ሔርማ ብለው ጠሩአት።

参见章节 复制




መሳፍንት 1:17
6 交叉引用  

አሳም ሊጋጠመው ወጣ፥ በመሪሳም አጠገብ ባለው በጽፋታ ሸለቆ ውስጥ ተሰለፉ።


በዚያም ተራራ ላይ የተቀመጡ አማሌቃውያንና ከነዓናውያን ወረዱ፥ አሸንፈወዋቸውም እስከ ሔርማ ድረስ አሳደዱአቸው።


ጌታም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፥ ከነዓናውያንንም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱንም ከተሞቻቸውንም እርም ብለው አጠፉ፤ የዚያንም ስፍራ ስም ሔርማ ብለው ጠሩት።


ኤልቶላድ፥ በቱል፥ ሔርማ፥


ይሁዳም ወንድሙን ስምዖንን፦ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ድርሻዬ ወደ ሆነው ምድር አብረን እንውጣ፤ እኔም እንደዚሁ ድርሻህ ወደ ሆነው ምድር አብሬህ እወጣለሁ” አለው። ስለዚህም ከእርሱ ጋር ሄደ።


በሖርማ፥ በቦርዓሻን፥ በዐታክና፥


跟着我们:

广告


广告