Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 9:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ አሉ፦ “ከሩቅ አገር መጥተናል፤ እንግዲህ አሁን ከእኛ ጋር የቃል ኪዳን አድርጉ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከዚያም ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ኢያሱንና የእስራኤልን ሰዎች፣ “የመጣነው ከሩቅ አገር ነው፤ ከእኛ ጋራ ቃል ኪዳን ግቡ” አሏቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ይህን ሁሉ ካደረጉ በኋላ በጌልገላ ወደሚገኘው ሰፈር ሄደው ኢያሱንና እስራኤላውያንን፦ “እኛ የመጣነው ከሩቅ አገር ነው፤ የመጣነውም ከእናንተ ጋር የቃል ኪዳን ውል ለማድረግ ነው” አሉአቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወደ ኢያ​ሱና ወደ እስ​ራ​ኤል ጉባኤ ወደ ጌል​ገላ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ “ከሩቅ ሀገር መጥ​ተ​ናል፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሰዎች፦ ከሩቅ አገር መጥተናል፥ አሁንም ከእኛ ጋር ኪዳን አድርጉ አሉ።

参见章节 复制




ኢያሱ 9:6
9 交叉引用  

“ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ፥ ግን ከስምህ ታላቅነት የተነሣ ከሩቅ የመጣ የባዕድ አገር ሰው ቢኖር፥


በዚያን ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሄዶ፥ “እነዚህ ሰዎች ከወዴት መጡ? ምንስ ነገሩህ?” ብሎ ጠየቀው። ሕዝቅያስም “እነርሱ የመጡት ባቢሎን ከሚባል ከሩቅ አገር ነው” ሲል መለሰለት።


ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ወደ ሰፈሩ ወደ ጌልገላ ተመለሱ።


የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው እንዲህ አሉት፦ “ባርያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፤ በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ አድነንም እርዳንም።”


ሕዝቡም በመጀመሪያው ወር በአሥረኛው ቀን ከዮርዳኖስ ወጡ፥ በኢያሪኮም ዳርቻ በምሥራቅ በኩል በጌልገላ ሰፈሩ።


የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ።


ያረጀና የተጠጋገነ ጫማ በእግራቸው አደረጉ አሮጌም ልብስ ለበሱ፤ ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀና የሻገተ ነበረ።


እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “ከአምላክህ ከጌታ ስም የተነሣ እጅግ ከራቀ አገር ባርያዎችህ መጥተናል፤ ዝናውንም፥ በግብጽም ያደረገውን ሁሉ፥


跟着我们:

广告


广告