Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 8:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ኢያሱም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ በሴቶቹም በሕፃናቱም በመካከላቸውም በሚኖሩት መጻተኞች ፊት ሙሴ ካዘዘው አንዲት ቃል እንኳ ሳያስቀር ሁሉን አነበበ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ኢያሱ በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ሴቶች፣ ሕፃናትና በመካከላቸው የኖሩ መጻተኞች ባሉበት ያነበበው፣ አንድም ሳይቀር ሙሴ ያዘዘውን ቃል ሙሉ በሙሉ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ኢያሱም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ በሴቶች፥ በሕፃናትና በመጻተኞች ፊት ሙሴ ካዘዘው ሕግ አንዲት ቃል እንኳ ሳያስቀር አነበበ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ኢያ​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ፥ በወ​ን​ዶ​ቹም፥ በሴ​ቶ​ቹም፥ በሕ​ፃ​ና​ቱም፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም በሚ​ኖ​ሩት መጻ​ተ​ኞች ፊት ሙሴ ካዘ​ዘው ያላ​ነ​በ​በ​ውና ያላ​ሰ​ማው ቃል የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ኢያሱም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ በሴቶቹም በሕፃናቱም በመካከላቸውም በሚኖሩት መጻተኞች ፊት ሁሉን አነበበ እንጂ ሙሴ ካዘዘው አንዲት ቃል አላስቀረም።

参见章节 复制




ኢያሱ 8:35
15 交叉引用  

ዕዝራ በእግዚአብሔር ቤት ፊት በግንባሩ ወድቆ እያለቀሰ በሚጸልይበትና በሚናዘዝበት ጊዜ፤ ወንዶች፥ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙበት እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፥ ሕዝቡም እጅግ አለቀሱ።


ካህኑ ዕዝራ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ሕጉን ወንዶች፥ ሴቶችና አስተውለው መስማት የሚችሉ ባሉበት በጉባኤው ሁሉ ፊት አመጣው።


በውኃው በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ፥ ወንዶች፥ ሴቶች፥ የሚያስተውሉም ባሉበት፥ ከማለዳ ጀመሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው፤ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ በጽሞና ያደምጥ ነበር።


ደግሞም ሌላ ብዙ ድብልቅ ሕዝብ መንጎችና ላሞችም እጅግ ብዙም ከብቶች ከእነርሱ ጋር ወጡ።


“ጌታ እንዲህ ይላል፦ በጌታ ቤት አደባባይ ቁም፥ በጌታም ቤት ውስጥ ለመስገድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ እንድትናገራቸው ያዘዝሁህን ቃላት ሁሉ ተናገር፤ አንዲትም ቃል አትጉድል።


ሕዝቡንም አከማቹ፥ ማኅበሩንም ቀድሱ፥ ሽማግሌዎቹንም ሰብስቡ፥ ሕፃናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ፥ ሙሽራው ከእልፍኙ፥ ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ።


የሠራዊት ጌታም እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከሁሉም የአሕዛብ ቋንቋ ዐሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና እኛም ከእናንተ ጋር እንሂድ” ይላሉ።


ኢየሱስም ይህን ሲያይ ተቆጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሏቸው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።


የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፤ ምንም አላስቀረሁባችሁም።


ጊዜውንም በፈጸምን ጊዜ ወጥተን ሄድን፤ ሁላቸውም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር እስከ ከተማው ውጭ ድረስ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ጸለይን፤


“እናንተ ሁላችሁ መሪዎቻችሁና አለቆቻችሁ፥ ሽማግሌዎቻችሁና ሹሞቻችሁ እንዲሁም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዛሬ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል፤


ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ፥ በሰፈራችሁም ያለ እንጨትህን የሚቆርጥ ውኃህንም የሚቀዳ መጻተኛ አብረውህ ቆመዋል።


ስለዚህ የምታደርጉት ሁሉ እንዲከናወንላችሁ የዚህን ኪዳን ቃሎች በጥንቃቄ ተከተሉ።


ይሰሙና ጌታ አምላካችሁንም መፍራት ይማሩ ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ በጥንቃቄ እንዲከተሉ ሕዝቡን ይኸውም ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና በከተሞችህ የሚኖረውንም መጻተኛ ሰብስብ።


እኔ ያዘዝኋችሁን የጌታ አምላካችሁን ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም፥ ከእርሱም አታጎድሉም።


跟着我们:

广告


广告