Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 7:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አካንም መልሶ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “በእውነት በእስራኤል አምላክ በጌታ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁ እንዲህና እንዲህም አድርጌአለሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 አካንም መልሶ ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “እውነት ነው! የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በድያለሁ፤ ያደረግሁትም ይህ ነው፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ዓካንም እንዲህ ሲል መለሰ፥ “እውነት ነው፤ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የበደልኩ እኔ ነኝ፤ እነሆ፥ ያደረግኹትም ከዚህ የሚከተለው ነው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 አካ​ንም መልሶ ኢያ​ሱን፥ “በእ​ው​ነት በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ያ​ለሁ፤ እን​ዲ​ህና እን​ዲ​ህም አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አካንም መልሶ ኢያሱን፦ በእውነት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በድያለሁ እንዲህና እንዲህም አድርጌአለሁ።

参见章节 复制




ኢያሱ 7:20
13 交叉引用  

እርስ በርሳቸውም፥ “ይኸው በወንድማችን ላይ ባደረስነው በደል ምክንያት ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማጠነን፥ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ።


እርሱም በሰው ፊት እየዘመረ፦ እኔ በድያለሁ፥ ቀናውንም አጣምሜአለሁ፥ የሚገባኝንም ቅጣት አልተቀበልሁም፥


ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደሆነ ምን ላድርግልህ? ስለምን እኔን ዒላማ አደረግኸኝ? ስለምን እኔ ሸክም ሆንሁብህ?


እኔስ ለመውደቅ ተቃርቤአለሁና፥ ቁስሌም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።


ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠራና እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ አምላካችሁንና እናንተን በደልሁ፤


ፈርዖንም ልኮ ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “በዚህ ጊዜ ኃጢአትን ሰርቻለሁ፤ ጌታ ጻድቅ ነው፥ እኔና ሕዝቤም በደለኞች ነን።


በለዓምም የጌታን መልአክ እንዲህ አለው፦ “ኃጢአትን ሠርቻለሁ፤ አንተ በመንገድ ላይ ልትቃወመኝ መቆምክን አላወቅሁም፤ እንግዲህም ይህ አሁን በፊትህ ክፉ የሆነ ነገር ቢሆን እመለሳለሁ።”


ይህ በብዙ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና።”


እንዲህም አለ “ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ።” እነርሱ ግን “ታዲያ እኛ ምን አገባን? ጉዳዩ የራስህ ነው፤” አሉት።


ኢያሱም አካንን እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ክብር ስጥ፥ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝ።”


በምርኮ መካከል አንድ ያማረ የሰናዖር ካባ፥ ሁለት መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም ኀምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፥ ወሰድኋቸውም፤ እነሆም፥ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፥ ብሩም ከሁሉ በታች ነው።”


ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ኃጢአት ሠርቼአለሁ፤ የጌታን ትእዛዝና የአንተን ቃል አልጠበቅሁም፤ ሕዝቡን በመፍራት የፈለጉትን ሁሉ አደረግሁ፤


ሳኦልም መልሶ፥ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ ነገር ግን በሕዝቤ አለቆች ፊትና በእስራኤል ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለጌታ እሰግድ ዘንድ እባክህ አብረኸኝ ተመለስ” አለው።


跟着我们:

广告


广告