Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በማግስቱም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ ለእስራኤል ልጆች መና አልመጣላቸውም፤ ነገር ግን በዚያው ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የምድሪቱን ፍሬ በበሉበት ቀን መናው መውረዱ ቀረ፤ ከዚያ በኋላ ለእስራኤላውያን መና አልወረደላቸውም፤ ነገር ግን በዚያ ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከምድሪቱ የሚገኘውን ምግብ መብላት ከጀመሩበት ቀን አንሥቶ መና መዝነቡን አቋረጠ፤ እስራኤላውያንም ከዚያን በኋላ ያን መና ማግኘት አልቻሉም፤ ከዚያን ጊዜ አንሥቶ በከነዓን የበቀለውን እህል መብላት ጀመሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በነ​ጋ​ውም ከም​ድ​ሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዳግ​መኛ መና አላ​ገ​ኙም፤ በዚ​ያው ዓመት የፊ​ኒ​ቆ​ንን ምድር ፍሬ ሰበ​ሰቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፥ ከዚያም በኋላ ለእስራኤል ልጆች መና አልመጣላቸውም፥ ነገር ግን በዚያው ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።

参见章节 复制




ኢያሱ 5:12
9 交叉引用  

የእስራኤልም ልጆች ወደሚኖሩባት ምድር እስኪመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ፤ ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስኪመጡ ድረስ መና በሉ።


ጻድቅ ሰው ለልጅ ልጆቹ ያወርሳል፥ የኃጢአተኛ ብልጥግና ግን ለጻድቅ ትጠበቃለች።


እናንተ የምድሪቱን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ለጌታ እንደ ልዩ ስጦታ የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ።


እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኋችሁ፤ ሌሎች ደከሙ፤ እናንተም እነርሱ በደከሙበት ገባችሁ።”


ከፋሲካውም በኋላ በማግስቱ የምድሪቱን ፍሬ እርሾ ያልገባበትን የቂጣ እንጎቻና ቆሎ በዚያው ቀን በሉ።


跟着我们:

广告


广告