Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከፋሲካውም በኋላ በማግስቱ የምድሪቱን ፍሬ እርሾ ያልገባበትን የቂጣ እንጎቻና ቆሎ በዚያው ቀን በሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከፋሲካም በኋላ በዚያ ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ማለት ቂጣና የተጠበሰ እሸት በሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በከነዓን የበቀለውን እህል መብላት የጀመሩትም በዚያን ቀን ማግስት ነበር፤ የተመገቡትም የተጠበሰ እሸትና ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከም​ድ​ሪ​ቱም ፍሬ ቂጣና አዲስ እህል በዚ​ያው ቀን በሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከፋሲካውም በኋላ በነጋው የምድሪቱን ፍሬ የቂጣ እንጎቻ ቆሎም በዚያው ቀን በሉ።

参见章节 复制




ኢያሱ 5:11
7 交叉引用  

የአምላካችሁን ቁርባን እስከምታመጡበት እስከዚህ ቀን ድረስ እንጀራውንም፥ የተጠበሰውንም እሸት፥ ለምለሙንም እሸት አትብሉ። ይህ በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።


በዚህም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን ለጌታ የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን እርሾ ያልነካው የቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ።


እናንተ የምድሪቱን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ለጌታ እንደ ልዩ ስጦታ የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ።


የእስራኤልም ልጆች በጌልገላ ሰፈሩ፤ ከወሩም በዓሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ።


በማግስቱም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ ለእስራኤል ልጆች መና አልመጣላቸውም፤ ነገር ግን በዚያው ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።


跟着我们:

广告


广告