Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 24:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ኢያሱም እነዚህን ቃላት በጌታ ሕግ መጽሐፍ ጻፈ፤ ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በጌታ መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ኢያሱም እነዚህን ቃሎች እግዚአብሔር የሕግ መጽሐፍ ጻፋቸው፤ ትልቅ ድንጋይም ወስዶ በባሉጥ ዛፍ ሥር፣ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ስፍራ አጠገብ አቆመው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ኢያሱም እነዚህን ትእዛዞች በእግዚአብሔር የሕግ መጽሐፍ ጻፈ፤ ከዚያም በኋላ አንድ ትልቅ ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ በሚገኘው የወርካ ዛፍ ሥር አቆመው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ኢያ​ሱም ይህን ቃል ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መጽ​ሐፍ ጻፈው፤ ኢያ​ሱም ታላ​ቁን ድን​ጋይ ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በነ​በ​ረ​ችው በአ​ሆማ ዛፍ በታች አቆ​ማት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ኢያሱም ይህን ቃል ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ጻፈ፥ ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው።

参见章节 复制




ኢያሱ 24:26
10 交叉引用  

ያዕቆብም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አቆመ።


እነርሱም በእጃቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ፥ እንዲሁም በጆሮአቸውም ያሉትን ጉትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፥ ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የባሉጥ ዛፍ በታች ቀበራቸው።


የርብቃ ሞግዚት ዲቦራም ሞተች፥ በቤቴልም ከባሉጥ ዛፍ በታች ተቀበረች፥ ስሙም “አሎንባኩት” ተብሎ ተጠራ።


ሙሴም የጌታን ቃሎች ሁሉ ጻፈ፤ በማለዳ ተነሥቶ ከተራራው በታች መሠዊያንና ዐሥራ ሁለት ሐውልቶች ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ።


የሴኬምና የቤትሚሎ ነዋሪዎች በሙሉ አቤሜሌክን ለማንገሥ ሴኬም ውስጥ በዐምዱ አጠገብ ካለው የባሉጥ ዛፍ ሥር ተሰበሰቡ።


ከዚህ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው፤ “ጌታ እስከ አሁን ድረስ ረድቶናል” ሲል ስሙን “አቤንኤዘር” ብሎ ጠራው።


跟着我们:

广告


广告