Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 23:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጌታ ታላላቆችንና ኃይለኞችን አሕዛብ ከፊታችሁ አሳድዶአቸዋል፤ እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “እግዚአብሔር ታላላቅና ኀያላን ሕዝቦችን ከፊታችሁ አሳድዶ አስወጥቷቸዋል፤ እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እናንተ ታላላቅና ብርቱዎች የሆኑትን ሕዝቦች እግዚአብሔር ነቃቅሎ አባሮላችኋል፤ እናንተን እስከ ዛሬ ድረስ ሊቋቋማችሁ የቻለ ማንም የለም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ላ​ቆ​ች​ንና ኀይ​ለ​ኞ​ችን አሕ​ዛብ ከፊ​ታ​ችሁ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ እስከ ዛሬም ድረስ የተ​ቋ​ቋ​ማ​ችሁ በፊ​ታ​ችሁ ማንም የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እግዚአብሔር ታላላቆችንና ኃይለኞችን አሕዛብ ከፊታችሁ አስወጥቶአል፥ እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም።

参见章节 复制




ኢያሱ 23:9
14 交叉引用  

በሚመጣውም ዓመት የአዴር ልጅ ሶርያውያንን አሰለፈ፥ ከእስራኤልም ጋር ይዋጋ ዘንድ ወደ አፌቅ ወጣ።


አምላካችን ሆይ! በዚህ ምድር የነበሩትን አሕዛብ ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት ያሳደድህ፥ ለወዳጅህም ለአብርሃም ዘር ለዘለዓለም የሰጠሃት አንተ አይደለህምን?


መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ ፌርዛውያን፥ ወደ ከነዓናውያን፥ ወደ ኤዊያውያንና ወደ እያቡሳውያን ያገባሃል፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ።


እስክትበዛና ምድርንም እስክትወርስ ድረስ በጥቂት በጥቂት አባርራቸዋለሁ።


አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች።


ከዚያም ጌታ እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል፤ እናንተም፥ ከእናንተ ይልቅ ታላላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ታስለቅቃላችሁ።


ነገሥታቶቻቸውንም በእጅህ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋለህ፤ እስክታጠፋቸው ድረስ ማንም ተቋቁሞህ በፊት ሊቆም አይችልም።


በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህምም።


ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴሲንና አኪመንን ተላሚንም ከዚያ ስፍራ አሳደደ። እነዚህም የዓናቅ ትውልድ ነበሩ።


ጌታ አምላካቸሁም እርሱ ከፊታችሁ በብርቱ ገፍቶ ያስወጣቸዋል፥ ከፊታችሁም ያሳድዳቸዋል፤ ጌታ አምላካችሁ እንደ ተናገራችሁም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።


እስከ ዛሬ ድረስ እንዳደረጋችሁት ግን ወደ አምላካችሁ ወደ ጌታ ተጠጉ።


ጌታ አሕዛብን ሁሉ፥ በምድሪቱ የተቀመጡትን አሞራውያን ከፊታችን አሳደደ፤ ስለዚህ እርሱ አምላካችን ነውና ጌታን እናገለግላለን።”


跟着我们:

广告


广告