ኢያሱ 22:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ጌታን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህል ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የአንድነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደሆነ ጌታ እርሱ ራሱ ይበቀለን፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 መሠዊያውን የሠራነው እግዚአብሔርን ከመከተል ወደ ኋላ ለማለት፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን ልናሳርግበት ወይም የኅብረት መሥዋዕት ልናቀርብበት አስበን ከሆነ፣ ራሱ እግዚአብሔር ይበቀለን። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ለእግዚአብሔር የማንታዘዝ ከሆንንና የሠራነውን መሠዊያ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባን፥ ወይም የአንድነት መሥዋዕት ልናቀርብበት አስበን ከሆነ ራሱ እግዚአብሔር ይቅጣን፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 አምላካችንን እግዚአብሔርን እንድንክደው፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህልን ቍርባን እንድናሳርግበት፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይመራመረን፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 እግዚአብሔርን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህል ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይበቀለን፥ 参见章节 |