Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 15:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ወደ ዓጽሞንም አለፈ፥ በግብጽም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንበሩም መጨረሻ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በዓጽሞን በኩል አድርጎም ወደ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ይገባና መቆሚያው ባሕሩ ይሆናል። እንግዲህ በደቡብ በኩል ያለው ወሰናቸው ይህ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ወደ ዓጽሞንም በመዝለቅ፥ በግብጽ ድንበር ላይ የሚገኘው ወንዝ፥ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይከተላል፤ ያም የድንበሩ መጨረሻ ይሆናል፤ እንግዲህ በደቡብ በኩል የይሁዳ ድንበር ይህ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ወደ አጽ​ሞ​ንም ያል​ፋል፤ በግ​ብ​ፅም ሸለቆ በኩል ይወ​ጣል፤ የድ​ን​በ​ሩም መውጫ በባ​ሕሩ አጠ​ገብ ነበረ፤ በደ​ቡብ በኩል ያለው ድን​በ​ራ​ቸው ይህ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ወደ ቀርቃ ዞረ፥ ወደ አጽሞንም አለፈ፥ በግብፅም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ፥ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው።

参见章节 复制




ኢያሱ 15:4
8 交叉引用  

በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፥


በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር።


ድንበርህንም ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረበዳ እስከ ወንዙ ድረስ አደርጋለሁ፤ በምድሪቱ የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፥ ከፊትህ ታባርራቸዋለህ።


በዚያ ቀን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ጌታ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።


ድንበሩም ከዓጽሞን ወደ ግብጽ ወንዝ ይዞራል፥ ባሕሩም ማብቂያው ይሆናል።


በግብጽ ፊት ለፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል እስካለችው የከነዓናውያን ሆና እስከ ተቈጠረችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን፥ የአስቀሎና፥ የጌት፥ የአቃሮን፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ናቸው፥ የኤዋውያን የሆኑትም እንዲሁ፥


ከዚያም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ወጣ፥ ወደ ጺንም አለፈ፥ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ወጣ፥ በሐጽሮንም በኩል አለፈ፥ ወደ አዳርም ወጣ፥ ወደ ቀርቃ ዞረ፥


አዛጦንና የተመሸጉና ያልተመሸጉ መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ያልተመሸጉም መንደሮችዋ፥ እስከ ግብጽ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ዳርቻ ድረስ።


跟着我们:

广告


广告