Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮናስ 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ይህ ወሬ ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፥ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ፥ ማቅ ለበሶ በአመድም ላይ ተቀመጠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ በደረሰ ጊዜ፣ ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱንም አወለቀ፤ ማቅም ለብሶ በዐመድ ላይ ተቀመጠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የነነዌ ንጉሥ ይህን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሰ መንግሥቱንም በማውለቅ ማቅ ለብሶ ዐመድ ላይ ተቀመጠ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወሬ​ውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እር​ሱም ከዙ​ፋኑ ተነ​ሥቶ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን አወ​ለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአ​መ​ድም ላይ ተቀ​መጠ።

参见章节 复制




ዮናስ 3:6
20 交叉引用  

የእስራኤልም ልጆች ተሰለፉ፥ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፥ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሾች የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፥ ሶርያውያን ግን ምድሩን ሞልተው ነበር።


ኢዮብም ሥጋውን ይፍቅበት ዘንድ ገል ወሰደ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ።


ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፥ በአፈርና በአመድ ላይ ተቀምጬ እጸጸታለሁ።”


በየመንገዳቸውም በማቅ ታጥቀዋል፤ በየሰገነቶቻቸውና በየአደባባዮቻቸው እንባ እጅግ እያፈሰሱ ሁሉም አልቅሰዋል።


ለንጉሡና ለንጉሥ እናት ለእቴጌይቱ፦ “የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ተዋርዳችሁ ተቀመጡ” በል።


ሚክያስም ባሮክ መጽሐፉን በሕዝቡ ጆሮ ባነበበ ጊዜ የሰማውን ቃላት ሁሉ ነገራቸው።


ንጉሡም ሆነ እነዚህን ቃላት ሁሉ የሰሙ ባርያዎቹ በጠቅላላ አልፈሩም ልብሳቸውንም አልቀደዱም።


የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ! ማቅ ልበሺ፥ በአመድም ውስጥ ተንከባለዪ፤ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለአንድያ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ፥ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።


ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፥ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፥ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ።


ተስፋ የሆነው እንደሆነ አፉን በአፈር ውስጥ ያኑር።


በዚያን ጊዜ የባሕር አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ያስቀምጣሉ፥ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፤ መንቀጥቀጥን ይለብሳሉ፥ በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ፥ በአንቺም ይደነቃሉ።


በጋት አታውሩት፥ በፍጹም አታልቅሱ፤ በቤትልዓፍራ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።


“ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን ኖሮ፥ ማቅ ለብሰው፥ አመድ ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበር።


“ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፥ ማቅ ለብሰው በአመድ ላይም ተቀምጠው፥ ገና ድሮ፥ ንስሐ በገቡ ነበር።


跟着我们:

广告


广告