Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮናስ 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፥ የምድር መወርወሪያዎችዋ ለዘለዓለም ተዘጉብኝ፤ ጌታ አምላኬ ሆይ አንተ ግን ሕይወቴን ከጉድጓድ አወጣሃት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሕይወቴ እየተዳከመ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔርን አስታወስኩ፤ ወደ አንተ ወደ አምላኬ ጸለይኩ፤ ጸሎቴም ወደ ቤተ መቅደስህ ወደ አንተ መጣ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራ​ሮች መሠ​ረት ወረደ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችዋ ወደ ተዘጉ ምድር ወረ​ድሁ፤ አቤቱ ፈጣ​ሪዬ! ሕይ​ወቴ ጥፋት ሳያ​ገ​ኛት ወዳ​ንተ ትውጣ።

参见章节 复制




ዮናስ 2:7
23 交叉引用  

ካህናቱና ሌዋውያኑም ተነሥተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምጻቸውም ተሰማ፥ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱስ መኖሪያው ወደ ሰማይ ዐረገ።


ጌታ በተቀደሰው መቅደሱ ነው፥ ጌታ፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፥ ዐይኖቹ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።


ሮሮዬን በፊቱ አፈስሳለሁ፥ መከራዬንም በፊቱ እናገራለሁ።


የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፥ የእጅህንም ሥራ አስተዋልሁ።


የሲኦል ገመዶች ተበተቡኝ፥ የሞት ወጥመዶችም ደረሱብኝ።


ጌታ የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ አወቅሁ፥ ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል፥ በቀኙ ብርታት ማዳን አለና።


እንደ ነጣቂና እንደሚያገሣ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ።


የጌታን ቸርነት በሕያዋን ምድር እንደማይ አምናለሁ።


ጠላቶቼ ሁልጊዜ፦ አምላክህ ወዴት ነው? ባሉኝ ጊዜ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ።


ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፥ በዓል የሚያከብሩ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።


ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።


የዓመፃ ነገር በረታብን፥ መተላለፋችንንስ አንተ ይቅር ትላለህ።


እነሆ፥ ታላቅ ምሬት ለደኅንነቴ ምክንያት ሆነ፤ አንተም ነፍሴን ከጥፋት ጉድጓድ አዳንካት፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጣልህ።


ከእናንተ ጌታን የሚፈራ፥ የአገልጋዩንም ቃል የሚሰማ፥ በጨለማም የሚሄድ፥ ብርሃንም የሌለው፥ ነገር ግን በጌታ ስም የሚታመን፥ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?


ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ልብ ጣልኸኝ፥ ወንዝም ከበበኝ፥ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ ላይ አለፉ።


ሕዝቦች ሆይ! ሁላችሁም ስሙ፤ ምድርና ሞላዋ ታድምጥ፤ ጌታ በቅዱስ መቅደሱ ሆኖ፥ ጌታ አምላክ በእናንተ ላይ ይመስክርባችሁ።


ጌታ ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ምድሪቷ ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።


በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኀጢአተኞች የደረሰበትን እንዲህ ያለውን ተቃውሞ እንዴት እንደተቋቋመ አስቡ።


ሰዎቹ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ነፍሳቸው ተማርራ ሊወግሩት ስለ ተመካከሩ ዳዊት በጣም ተጨነቀ፤ ነገር ግን ዳዊት በአምላኩ በጌታ በረታ።


跟着我们:

广告


广告