Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮናስ 1:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እንዲህም አሉት፦ “እባክህ ንገረን፥ ይህ ክፉ ነገር በምን ምክንያት መጣብን? ሥራህ ምንድነው? ከወዴት መጣህ? አገርህስ የት ነው? የየትኛው ሕዝብ ወገን ነህ?”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም፣ “ይህ ሁሉ አስጨናቂ ነገር በማን ምክንያት እንደ መጣብን ንገረን፤ ሥራህ ምንድን ነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህስ የት ነው? ከየትኛውስ ሕዝብ ነህ?” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለዚህ ዮናስን “እስቲ ንገረን! ይህ ሁሉ አደጋ የመጣብን በማን ምክንያት ይመስልሃል? ለመሆኑ ሥራህ ምንድን ነው? ከወዴት መጣህ? አገርህስ የት ነው? የየትኛው ሕዝብ ወገን ነህ?” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የዚ​ያን ጊዜም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ገ​ኘን እባ​ክህ ንገ​ረን፤ ሥራህ ምን​ድን ነው? ከወ​ዴ​ትስ መጣህ? ወዴ​ትስ ትሄ​ዳ​ለህ? ሀገ​ርህ የት ነው? ወገ​ን​ህስ ምን​ድን ነው?” አሉት።

参见章节 复制




ዮናስ 1:8
5 交叉引用  

ፈርዖንም ወንድሞቹን፦ “ሥራችሁ ምንድነው?” አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፦ “እኛ አገልጋዮችህ፥ እኝም አባቶቻችንም፥ በግ አርቢዎች ነን” አሉት።


ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።


ኢያሱም አካንን እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ክብር ስጥ፥ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝ።”


ከዚያም ሳኦል ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ነገር ንገረኝ” አለው። ዮናታንም፥ “በበትሬ ጫፍ ጥቂት ማር ቀምሻለሁ፤ እነሆኝ፥ ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለው።


ዳዊትም፥ “አንተ የማን ነህ? የመጣኸውስ ከየት ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም እንዲህ አለው፤ “እኔ ግብፃዊ ስሆን፥ የአንድ አማሌቃዊ አገልጋይ ነኝ፤ ከሦስት ቀን በፊት ታምሜ በነበረበት ጊዜ ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።


跟着我们:

广告


广告