Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 5:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሰውዬው ሄዶ ያዳነው ኢየሱስ እንደሆነ ለአይሁድ ነገረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሰውየውም የፈወሰው ኢየሱስ መሆኑን ሄዶ ለአይሁድ ነገራቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሰውየውም ሄደና ያዳነው ኢየሱስ መሆኑን ለአይሁድ ባለሥልጣኖች ነገረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ያም ሰው ሄዶ ያዳ​ነው ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እንደ ሆነ ለአ​ይ​ሁድ ነገ​ራ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሰውዬው ሄዶ ያዳነው ኢየሱስ እንደ ሆነ ለአይሁድ ነገረ።

参见章节 复制




ዮሐንስ 5:15
12 交叉引用  

ሰውየው ግን በሄደበት ሁሉ ነገሩን በሰፊው አወራ፤ ወሬውንም አሠራጨ፤ በዚህ ምክንያት ኢየሱስ ወደ ማንኛውም ከተማ በግልጽ መግባት አልተቻለውም፤ ከዚህም የተነሣ ከከተማ ውጭ በሚገኙ ሰዋራ ቦታዎች መኖር ጀመረ፤ ሰዎች ግን ከየአቅጣጫው እርሱ ወዳለበት ይመጡ ነበር።


አይሁድም “አንተ ማን ነህ?” ብለው ለመጠየቅ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።


“ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?” አለች።


ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው “ሰንበት ነው፥ አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም፤” አሉት።


እነርሱም “‘አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፤’ ያለህ ሰው ማን ነው?” ብለው ጠየቁት።


ስለዚህም አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር፤ በሰንበት ይህን አድርጎ ነበርና።


እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ደግሞ እራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ “እግዚአብሔር አባቴ ነው፤” ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።


ስለዚህ ፈሪሳውያን እንዴት እንዳየ እንደገና ጠየቁት። እርሱም “ጭቃ በዐይኖቼ አኖረ፤ ታጠብሁም፤ አያለሁም፤” አላቸውም።


እርሱም መልሶ “ኀጢአተኛ መሆኑን አላውቅም፤ ዐይን ሥውር እንደ ነበርሁ፥ አሁንም እንደማይ፥ ይህንን አንድ ነገር አውቃለሁ፤” አለ።


ሰውዬው መለሰ፤ እንዲህም አላቸው “ከወዴት እንደሆነ እናንተ አለማወቃችሁ ይህ ድንቅ ነገር ነው፤ ዳሩ ግን ዐይኖቼን ከፈተ።


መልሰው “አንተ ሙሉ በሙሉ በኃጢአት ተወልድህ፤ እኛን ታስተምረናለህን?” አሉት። ወደ ውጭም አወጡት።


跟着我们:

广告


广告