Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዩኤል 2:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ታላቁና የሚያስፈራው የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ፀሓይ ወደ ጨለማ፤ ጨረቃም ወደ ደም ትለወጣለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ታላቁና አስፈሪው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ደም ትመስላለች፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ታላ​ቋና ግልጥ የሆ​ነ​ችው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ሳት​መጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረ​ቃም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል።

参见章节 复制




ኢዩኤል 2:31
21 交叉引用  

ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፥ በላይም ሰማይ ይጠቁራል፤ ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከእርሱም አልመለስም።”


በማጠፋህ ጊዜ ሰማዮችን እሸፍናለሁ፥ ከዋክብቶቻቸውንም አጨልማለሁ፤ ፀሐይን በደመና እሸፍናለሁ፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም።


የጌታ ቀን መጥቷልና፥ እርሱም ቀርቧልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ።


ምድሪቱም ከፊታቸው ትናወጣለች፥ ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፥ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ።


ጌታም በሠራዊቱ ፊት ድምፁን ያሰማል፥ ሠራዊቱ እጅግ ብዙ ነውና፥ ቃሉንም የሚፈጽም እርሱ ኃያል ነውና፥ የጌታ ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነውና ማንስ ይችለዋል?


የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፥ ከዘለዓለምም ጀምሮ እንደ እነርሱ ያለ አልነበረም፥ ከእነርሱም በኋላ ለብዙ ትውልድ እንደ እነርሱ ያለ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም።


እነሆም፥ በዚያ ወራትና በዚያ ዘመን፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮ በምመልስበት ጊዜ፥


ፀሐይና ጨረቃ ጨልመዋል፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ሰውረዋል።


በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ አይኖርም።


“እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ ሥርንና ቅርንጫፍንም አያስቀርላቸውም።


እነሆ፥ ታላቁና አስፈሪው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።


“ከነዚያ ቀናት መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይሎችም ይናወጣሉ።


ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።


“በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ላይ ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ በመረበሽ ይጨነቃሉ፤


ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።


አራተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፤ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንና የሌሊት ሲሶው እንዳያበራ ተከለከለ።


跟着我们:

广告


广告