Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 37:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በረዶውንና ውሽንፍሩን ብርቱንም ዝናብ፦ በምድር ላይ ውደቁ ይላል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በረዶውን፣ ‘በምድር ላይ ውደቅ’ ውሽንፍሩንም ‘ዶፍህን አውርደው’ ይላል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በረዶ በምድር ላይ እንዲወርድ ያደርጋል፤ ብርቱ ዝናብም እንዲዘንብ ያዛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በረ​ዶ​ው​ንና ውሽ​ን​ፍ​ሩን፥ ብር​ቱ​ው​ንም ዝናብ በም​ድር ላይ እን​ዲ​ወ​ርድ ያዝ​ዛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በረዶውንና ውሽንፍሩን ብርቱንም ዝናብ፦ በምድር ላይ ውደቁ ይላል።

参见章节 复制




ኢዮብ 37:6
14 交叉引用  

ነገር ግን ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ጊዜውም የዝናብ ጊዜ ነው፥ በውጭ ልንቆም አንችልም፥ በዚህ ነገር እጅግ ተላልፈናልና ይህ ሥራ የአንድ ወይም የሁለት ቀን ሥራ አይደለም።


በሦስት ቀን ውስጥ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ።


ለዝናብም ሥርዓትን፥ ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን ባደረገ ጊዜ፥


የውኃውን ነጠብጣብ ወደ ላይ ይስባል፥ ዝናብም ከጉም ይንጠባጠባል፥


በውኑ ወደ በረዶው ቤተ መዛግብት ገብተሃልን? የበረዶውንስ ቤተ መዛግብት አይተሃልን?


በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ በእርሻም ላይ ውኃ ይልካል።


እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥ ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥


ድሆችን የሚያስጨንቅ ድሃ ሰው እህልን እንደሚያጠፋ እንደ ዶፍ ዝናብ ነው።


በኖራ የሚቀቡትን እንዲህ በላቸው፦ ይወድቃል፤ ዶፍ ዝናብ ይዘንባል፥ ታላቅም የበረዶ ድንጋዮች ይወድቃሉ፥ ዐውሎ ነፋስም ይሰነጣጥቀዋል።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመዓቴ በዐውሎ ነፋስ እሰነጣጥቀዋለሁ፥ በቁጣዬም ዶፍ ዝናብ፥ በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ሊያጠፋው ይወርዳል።


አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ጠፈሩንም በምድር ላይ የመሠረተ፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሰው እርሱ ነው፤ ስሙም ጌታ ነው።


跟着我们:

广告


广告