Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 36:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ብልጽግናህና ኃይልህ በሙሉ ከችግር የሚጠብቅህ ይመስልሃልን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ባለጠግነትህም ሆነ ብርቱ ጥረትህ ሁሉ፣ ችግር ውስጥ እንዳትገባ ሊረዳህ ይችላልን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሀብትህና ሥልጣንህ ምንም ያህል ከፍተኞች ቢሆኑ፥ ከጭንቀት አያድኑህም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በጭ​ን​ቀት ካሉ ከች​ግ​ረ​ኞች ልመና የተ​ነሣ አእ​ም​ሮህ በፈ​ቃድ አያ​ስ​ትህ

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ባለጠግነትህ የኃይልህም ብርታት ሁሉ ያለ ችግር እንድትሆን ሊረዳህ ይችላልን?

参见章节 复制




ኢዮብ 36:19
13 交叉引用  

እነርሱ በእኩለ ሌሊት በድንገት ይሞታሉ፥ ሕዝቡ ተንቀጥቅጦ ያልፋል፥ ኃያላንም ያለ ምንም ድካም ይወገዳሉ።


ሀብት ወደ ስድብ አስቶ እንዳይወስድህ፥ ትልቅ ጉቦም ከመስመር እንዳያስወጣህ።


ሰዎች ድንገት የሚሞቱበትን ሌሊትን አትመኛት።


“እግዚአብሔር ቁጣውን አይመልስም፥ ከእርሱ በታች ረዓብን የሚረዱ ይዋረዳሉ።


በኃይላቸው የሚታመኑ፥ በሀብታቸውም ብዛት የሚመኩ፥


በክፋት የተገኘ መዝገብ ጥቅም የለውም፥ ጽድቅ ግን ከሞት ያድናል።


ክፉ ሰው በእርግጠኛነት ሳይቀጣ አይቀርም፥ የጻድቃን ዘር ግን ይድናል።


በቁጣ ቀን ሀብት አትረባም፥ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች።


በዚያን ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፤ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።


የጌታም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።


በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና።


ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጎአል፤ ዝገቱም በእናንተ ላይ ይመሰክራል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል፤ ለመጨረሻው ዘመን ሀብትን አከማችታችኋል።


跟着我们:

广告


广告