Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 31:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ነገር ግን ነፍሱ እንዲጠፋ በመራገም አንደበቴ ኃጢአት እንዲሠራ አልፈቀድሁም፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እኔ ግን በነፍሱ ላይ ክፉ እንዲመጣ በመራገም፣ አንደበቴን ለኀጢአት ከቶ አሳልፌ አልሰጠሁም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ‘ጠላቶቼ ይጥፉ’ ብዬ በመራገም ኃጢአት ከቶ አልሠራሁም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ጆሮዬ መር​ገ​ሜን ትስማ፤ በወ​ገ​ኔም መካ​ከል ክፉ ስም ይው​ጣ​ልኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ነገር ግን በመርገም ነፍሱን በመሻት አንደበቴን ኃጢአት ይሠራ ዘንድ አልሰጠሁም፥

参见章节 复制




ኢዮብ 31:30
13 交叉引用  

አላዋቂውን ሰው ሥር ሰድዶ አየሁት፥ ድንገትም መኖሪያውን ረገምሁ።


አቤቱ አምላኬ፥ እንዲህ አድርጌ ከሆነ፥ ዓመፃም በእጄ ቢኖር፥


ሕልም በሥራ ብዛት ይታያል፥ እንዲሁም የአላዋቂም ድምፅ በቃሉ ብዛት ይሰማል።


ብዙ ሕልም ባለበት፥ እንዲሁም ብዙ ቃል ባለበት፥ ብዙ ከንቱ ነገር አለ፥ አንተ ግን እግዚአብሔርን ፍራ።


እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ከንቱ ቃል ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤


እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙን ‘የማያስብ’ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ‘ደደብ’ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።


የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ።


ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች።


ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም በረከትን ልትወርሱ ተጠርታችኋል።


跟着我们:

广告


广告