Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 31:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ልዑል እግዚአብሔርን በካድሁ ነበርና፥ ይህ ደግሞ በፈራጆች የሚያስቀጣ በደል በሆነ ነበር።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ለልዑል እግዚአብሔር ታማኝ አለመሆኔ ነውና፣ ይህም ደግሞ የሚያስቀጣኝ በደል በሆነ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ይህን ማድረግ በላይ ለሚገኘው አምላክ እምነተቢስነት ስለ ሆነ፥ እነዚህ ድርጊቶች የሞት ፍርድ የሚያመጡ ኃጢአቶች ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 በል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዋ​ሸሁ ነበ​ርና ይህ ደግሞ ትልቅ በደል ይሁ​ን​ብኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ልዑል እግዚአብሔርን በካድሁ ነበርና ይህ ደግሞ ፈራጆች የሚቀጡበት በደል በሆነ ነበር።

参见章节 复制




ኢዮብ 31:28
19 交叉引用  

ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”


አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም ጮኾ በአበኔር መቃብር ላይ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ።


የሚከራከረው ቅን ሰው መሆኑን ይመሰክር ነበር፥ እኔም በፈራጅ ፊት ለዘለዓለም ነፃ እወጣ ነበር።”


ይህ ክፉ አበሳ፥ ፈራጆችም የሚቀጡበት በደል ነውና፥


ልቤ በስውር ተታልሎ፥ አፌም እጄን ስሞ እንደሆነ፥


ጻድቅ ብሆንም እንኳን ልመልስለት አልችልም፥ ፈራጄን እማጸናለሁ እንጂ።


ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።


እንዳልጠግብ እንዳልክድህም፦ “ጌታስ ማን ነው?” እንዳልል፥ ድሀም እንዳልሆን እንዳልሰርቅም፥ የአምላኬንም ስም እንዳላረክስ።


ዐምፀናል፥ ሐሰትን ተናግረናል፥ ጌታን ከመከተል ተመልሰናል፤ ግፍንና ዓመፅንም ተናግረናል፥ የኃጢአት ቃልንም ፀንሰን ከልብ አውጥተናል።


ወደ ሌዋውያን ካህናት በዚያም ዘመን ወደ ተሾመው ፈራጅ መጥተህ ትጠይቃለህ፥ እነርሱም የፍርዱን ነገር ይነግሩሃል።


እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ በግልጥ ይናገራሉ ዳሩ ግን በሥራቸው ይክዱታል፤ የሚያጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ ብቁ ያልሆኑ ናቸው።


በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥


እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “አሁን እንግዲህ በመካከላችሁ ያሉትን እንግዶች አማልክት አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ ጌታ አዘንብሉ።”


ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ የተናገረንን የጌታን ቃል ሁሉ ሰምቶአልና ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል፤ እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል።”


ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይኖራሉ፤ እነርሱም ጥፋትን የሚያስከትሉ ትምህርቶች አስርገው በማስገባት የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፥ በራሳቸው ላይ ፈጣን ጥፋትን ያመጣሉ።


ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ የለውም፤ በወልድ የሚያምን አብ አለው።


አስቀድሞ ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በዝሙት ይለውጣሉ፤ ብቸኛ ንጉሣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።


እኔ አልበደልሁህም፤ አንተ ግን በእኔ ላይ ዘምተህ በድለኸኛል፤ እንግዲህማ ፈራጅ የሆነው ጌታ በእስራኤላውያንና በአሞናውያን መካከል ዛሬ ይፍረድ።”


跟着我们:

广告


广告